አባይ ሚዲያ ዜና – ጥር 6፣2012

በመሳፍንት ዘመን ተበታትና የነበረችው ኢትዮጵያን አንድ ለማድረግ እንደለፉ ታሪክ የማይረሳቸው አጼ ተዎድሮስ በዛሬው እለት ጥር 6/1811 ዓ/ም መወለዳቸውን ይታወሳል።

ይህንንም ተከትሎ በተለያዩ የአማራ ክልል ከተሞች በተለይም በደብረታቦርና በጎንደር ከተሞች በተለያዩ ትምህርት ቤቶችና ኮሌጆች የንጉሡ 201ኛ የልደት በዓል እየተከበረ ይገኛል።

አጼ ቴዎድሮስ በበጌምድር ተወልደው ከ1847 እስከ ህልፈተ ህይወታቸው 1860 ዓ/ም ኢትዮጵያን ያስተዳደሩና ዘመናዊ የኢትዮጵያ ወታደርን ጨምሮ የውጭ ግንኙነትን የመሰረቱ ታላቅ ሰው እንደነበሩ የታሪክ መዛግብት ያስረዳሉ።

ንጉሱ የልጅነት ስማቸው ካሣ ኃይሉ ይባል የነበረ ሲሆን በ1860 ዓ/ም መቅደላ ላይ ከእንግሊዝ ጋር በነበራቸው ጦርነት እጃቸውን ለጠላት ላለመስጠት ሲሉ ራሳቸውን ማጥፋታቸውንም ታሪካቸው ይገልጻል።