አባይ ሚዲያ ዜና – ጥር 8፣ 2012

በዩኒቨርሲቲው የኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክተር አቶ ተፈራ አስናቀ እንዳረጋገጡት ሶስቱ ምክትል ፕሬዝዳንቶች የታገዱት በዩኒቨርሲቲው ሴኔት ውሳኔ መሰረት ነው።

ምክትል ፕሬዝዳንቶቹ የታገዱት ቀደም ሲል ያጋጠሙ ግጭቶችን ተከትሎ የደረሰውን ጉዳት ለመቆጣጠርና ኃላፊነታቸውን ለመወጣት ጥረት እንዳላደረጉ በሚል በመገምገሙ እንደሆነ ከዩኒቨርስቲው ያገነኘው መረጃ ያመለክታል።

የወልዲያ ዩኒቨርሲቲ ካለፈው ህዳር ወር መጨረሻ ጀምሮ የመማር ማስተማር ስራው ላይ አለመረጋጋት ገጥሞት እንደቆየ ይታወቃል።