አባይ ሚዲያ ዜና -ጥር 9፣2012

በአሜሪካ የሚኖሩ የቀድሞ የፋሲለደስ ከፍተኛ መሰናዶ ትምህርት ቤት ተማሪዎች የትምህርት ቤቱን የመማሪያ ክፍል ጥበት ችግር ለመቅረፍ ከ20 ሚሊየን ብር በላይ በሆነ ወጪ ባለ ሁለት ደርብ ህንጻ ለመገንባት የመሰረት ድንጋይ አኖሩ።

የመማሪያ ክፍል ህንጻው በሶስት አመት ጊዜ ውስጥ ይጠናቀቃል ተብሏል።

ትምህርት ቤቱ ከተማሪዎች ቁጥር መጨመር ጋር በተያያዘ በአንድ ክፍል 100 በላይ ተማሪዎችን ለማስተማር እንተገደደ ተገልጿል።