አባይ ሚዲያ ዜና -ጥር 9፣2012

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን የሀድያና ስልጤ ሀገረ ስብከት መጭውን የጥምቀት በዓል ለማክበር የሚያስችል ቦታ በሆሳዕና ከተማ አላገኘንም ሲል መግለጫ አውጥቷል፡፡

መግለጫው እንደሚያትተው ከአሁን በፊት የጥምቀት በዓልን የምናከብርበት ቦታ የቤተ ክርስቲያን የይዞታ መሬት ሳይሆን የገበያ ቦታ በመሆኑ እና ቤተ ክርስቲያን ያላትን ቦታ እንድንጠቀም በተደጋጋሚ ለሆሳዕና ከተማ አስተዳደርና ለሀድያ ዞን አስተዳደር ብናቀርብም መፍትሄ ባለማግኘታችን የጥምቀት በዓልን የምናከብርበት ቦታ አጥተናል ብሏል፡፡

በመሆኑም ምዕመኑ እስከ 08/05/2012 ዓም ድረስ በጉጉት ሲጠብቁ እንደነበር ገልጾ መፍትሄ ሊሰጥ ባለመቻሉ ከፍተኛ የሆነ የጸጥታ ስጋት ውስጥ ስለምትገኝ የሀድያና ስልጤ ሀገረ ስብከት፣ የሆሳዕና ከተማ ስምንቱም ርእሰ አድባራትና ዲያቆናት በዓሉ በአደባባይ እንዳይከበር ውሳኔ ማሳለፋቸውን ገልጸዋል፡፡