አባይ ሚዲያ ዜና -ጥር 9፣2012

በዛሬው ዕለት ሊቆም የነበረው የቅዱስ ያሬድ አደባባይ ምንም እንኳን ከፍተኛ ውዝግብ ሲያስነሳ የቆየ ቢሆንም በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመንገዶች ባለስልጣን መንገዱን ያልተረከበ በመሆኑ የአደባባዩን ልኬት በውል አላወኩትም ብሏል፡፡

በዚህም በአካባቢው ወጣቶችና በከተማ አስተዳደሩ መካከል ውዝግብ ሲያስነሳ የቆየ ሲሆን  የሀውልት ተከላ ባይደረግም የአደባባይ ቅድመ ምረቃ ተደርጓል፡፡

በምረቃ ስነ ስርዓቱ ላይ ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ከፍተኛ ባለድርሻዎችን ጨምሮ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የባህል እና ቱሪዝም ቢሮ ሃላፊዎች ተገኝተዋል፡፡

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን የውጭ ግንኙነት ሃላፊ ብጹዕ አቡነ አረጋዊ (ዶ/ር) እንደገለጹት ታሪክ ያላቸውን አባቶች እና ኢትዮጵያዊያንን ማሰብና መዘከር ተገቢ እንደሆነ አስገንዝበዋል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የባህልና ቱሪዝም ቢሮ ሃላፊ ረዳት ፕሮፌሰር ነብዩ ባዩ እንደገለጹት የቅዱስ ያሬድ መታሰቢያ አደባባይ ለአካባቢው ብቻ ሳይሆን ለአለም ማህበረሰብ መታሰቢያ ነው ብለዋል፡፡