አባይ ሚዲያ ዜና -ጥር 13፣2012

ምክትል ከንቲባ ኢንጂነር ታከለ ኡማ ወደ ሥልጣን ከመጡ ወዲህ ካስተላለፏቸው ውሳኔዎች መካከል፤ መሬት ለአዲስ አልሚዎች በጨረታ የሚተላለፍበት ሥርዓት ላይ ያለው የአሠራር ችግር ተጠንቶ እስኪቀረፍ ድረስ መሬት በጨረታ እንዳይቀርብ የሚለው ይገኝበታል።

ይህ ውሳኔ ለረዥም ጊዜ ሳይነሳ መቆየቱ በበርካታ መሬት ፈላጊ ባለሀብቶች ላይ ቅሬታ መፍጠሩ ይታወሳል።

የአስተዳደሩ ከንቲባ ጽሕፈት ቤት ሰሞኑን ባወጣው መረጃ፤ ተቋርጦ የነበረውን የሊዝ ጨረታ ለመጀመር አስፈላጊው ዝግጅት መገባደዱን አስታውቋል።

እንደ አዲስ በሚጀመረው የሊዝ ጨረታ የሚቀርቡ 100 የተለያየ መጠን ያላቸው የመሬት ይዞታዎች፤ በአንድ ጊዜ እንደሚቀርቡም ለማወቅ ተችሏል ሲል ሪፖርተር አስነብቧል።