አባይ ሚዲያ ዜና -ጥር 13፣2012

በቤኔሻንጉል ጉሙዝ ክልል ወምበራ ወረዳ ኮንግ ቀበሌ ማዕከል ጥር 8/2012 ከቀኑ 10 ሰአት በተፈጸመ ጥቃት የሰዎች ሕይወት ማለፉን ፌዴራል ፖሊስ አረጋግጧል፡፡

ከጥር 11 ጀምሮ የመከላከያ ሰራዊት ወደ አካባቢው ገብቶ እያረጋጋ እንደሆነ በፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን የመተከልና አዊ ብሔረሰብ አካባቢዎች አዛዥ ዋና ኢንስፔክተር ኢብራሂም ሙሃመድ ገልጸዋል፡፡

በአካባቢው ነዋሪዎች በተፈጸመው ጥቃት የሦስት ሰዎች ህይዎት ማለፉን ዋና ኢንስፔክተሩ ቢናገሩም የአካባቢው ነዋሪዎች ግን የሟቾች ቁጥር ከዛም እንደሚበልጥ ይናገራሉ፡፡ ጥቃቱን ምክንያት ለማወቅና ተርጣሪዎችን ለመያዝ ጥረት እያደረጉ እንደሆነ ዋና ኢንስፔክተር ኢብራሂም ተናግረዋል፡፡