አባይ ሚዲያ ዜና -ጥር 13፣2012

የከተማዋ ምክትል ከንቲባ ኢንጂነር ታከለ ኡማ በዚህ ሳምንት የሚያደርጉትን ሹምሽር ለከተማ አስተዳደሩ ምክር ቤት አቅርበው እንደሚያፀድቁ፣ ከታማኝ ምንጮች የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

ይነሳሉ ተብለው ከሚጠበቁት ውስጥ ምክትል ከንቲባና የትራንስፖርት ቢሮ ኃላፊው ዶ/ር ሰለሞን ኪዳኔን ጨምሮ የመሬት አስተዳደር፣ እንዲሁም የከተማው ፕላንና ልማት ኮሚሽን ኃላፊዎችና ሌሎችም መሆናቸው ታውቋል።

በመሬት አስተዳደር ላይ የሚደረገው ሹምሽር መጠነ ሰፊ እንደሚሆን የገለጹት ምንጮች የዚህ ምክንያቱ ደግሞ በከተማዋ በተለያዩ ጊዜያት የሚከናወኑ የመሬት ወረራዎች መሆናቸውን ገልጸዋል።

ከሰሞኑ ይካሄዳል ተብሎ በሚጠበቀው ሹምሽር የሚነሱትን ኃላፊዎች በመተካት የአፋር፣ የሶማሌና የሐረሪ ተወላጆች የካቢኔ አባል ሆነው የሚሾሙ ሲሆን በአዲሱ ካቢኔ የሚካተቱት አብዛኞቹ አዲስ አበባ የተወለዱና የኖሩ መሆናቸውም ተገልጿል፡፡