አባይ ሚዲያ ዜና – ጥር 14፣2012

የህዝባዊ ወሓነ ሓርነት ትግራይ የህወሓትና የኢህአዴግ ስራ አስፈጻሚ አባልና የቀድሞ ታጋይ የነበሩት ወ/ሮ ፈትለወርቅ ገ/እግዚአብሔር (ሞንጀሪኖ) በትላንትናው እለት ከንግድ ሚኒስቴር ሹመታቸው መሻራቸውንና መንግስት ሌሎች አዳዲስ ሚኒስትሮች ስለመሾሙን በዜና እወጃችን ማሳወቃችን ይታወሳል።

ይህንን ተከትሎም ህወሓት ሚኒስትሯ ወ/ሮ ፈትለወርቅ ገ/እግዚአብሄርና ሌሎች በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የነበሩ ሹመኞች በትግራዋይነታቸው ነው የተሻሩት ሲል ህወሓት ተቃውሞውን በመግለጫ ገልጿል።

በዛሬው እለትም የሚኒስትሯን ከስልጣን መውረድ ያስቆቸው ህወሓት በክልሉ የኮምዩኒኬሽን ቢሮ ይፋዊ ድህረገጹ “ፅናዓት ንዘይተርፍ ዓወት” ጽናት ላይቀር ድል” ሲል አስፈራርቷል።

ይሁን እንጅ ከስልጣናቸው የተሻሩት ወ/ሮ ፈትለወርቅ ገ/እግዚአብሄር በንግድ ሚኒስቴር የስልጣን ቆይታቸው በወልቃይትና ሁመራ አካባቢ የሚገኙ የሰሊጥ አምራቾችና ነጋዴዎችን ማክሰራቸውን የአካባቢው ምንጮቻን ገልጸውልናል።

ትእምት (EFFORT) የሚባል ትልቅ የንግድ ድርጅት  በ1977 ዓ/ም በውጭ ሃገራት ለምነን ካጠራቀምነው ገንዘብ ያቋቋምነው ነው እሚሉት ህወሓቶች የኢትዮጵያ ህዝብ ደግሞ የሃገር ገንዘብ ነው ብሎ እሚያምነውን ሲሆን የዚህ ድርጅት እህት ኩባንያዎች የሆኑት ጉና~ኢትዮጵያንና ህይወት የእርሻ መካናይዜሽን ባለፉት 2 ዓመታት በወልቃይት ጸገዴና ሰሜን ጎንደር-አብደራፊን የሰሊጥና ሌሎች ጥራጥሬ ምርቶችን በወ/ሮ ፈትለወርቅ ቀጥተኛ ትእዛዝ የንግዱን ማህበረሰብንና አምራች ገበሬዉን ሲያከስሩ መቆየታቸውን ሰምተናል።

ከዚህ ጋር ተያይዞም በዚህ ዓመት የሰሜን ጎንደር ዞን አብደራፊ ከተማ የሰሊጥ አምራቾችና ነጋዴዎች አሁን የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ሆነው በተሾሙት አቶ መላኩ አለበል ሰብሳቢነት በንግድና ኢንዱስትሪ አማካኝነት ህዝቡንና አገሪቱን ያጋጠማቸው የንግድና የውጭ ምንዛሬ ኪሳራ ይፋ አድርገው እንደነበር ይታወሳል።

ሰሚ አጥተው እንደቆዩ ያብራሩልን ምንጮች ሚኒስትሯ ድርጅታቸው ኢፈርትን ለመርዳት ሲሉ ህጋዊ ምርቶችን በህገወጥ መንገድ ወደ ሱዳን አገር ያለ አገሪቱ ፈቃድ ሲልኩ እንደነበርና ይህንንም የንግዱ ማህበረሰብንና ሰሊጥ አምራቾችን ከመጉዳቱ በተጨማሪ አገሪቱንም ለውጭ ምንዛሬ እጦትና ለትልቅ ኪሳራ ዳርጓት ነበር ሲሉ አብራርተዋል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ ህወሓት ያወጣውን መግለጫ በተመለከተ የብልጽግና ፓርቲ ወ/ሮ ፈትለወርቅ ገ/እግዚአብሔር ከስልጣናቸው የተሰናበቱት የትግራይ ተወላጅ በመሆናቸው ሳይሆን የሚኒስቴር ጽህፈት ቤቱ ባወጣው የስራ ሽግሽግ ምደባ ነው ሲል የብልጽግና ፓርቲ አስታውቋል።