አባይ ሚዲያ ዜና – ጥር 14፣2012

የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ የ2012 የምርጫ ማስፈጸሚያ የጊዜ ሰሌዳን ለውይይት ይፋ ሲያደርግ የፖለቲካ ፓርቲዎችም የመጀመሪያ ዙር ውይይት አድርገውበታል።

በዚሁ ውይይታቸውም ዘርዝረው ባቀረቧቸው ምክንያቶች የተነሳ የጊዜ ሰሌዳውን የደገፉም የተቃወሙም ፓርቲዎች መኖራቸው ግልጽ ሆኗል።

አቶ በቀለ ገርባ የኦሮሞ ፌዴራላዊ ኮንግረስ ፓርቲ (ኦፌኮ) ተቀዳሚ ምክትል ሊቀመንበር ናቸው።

የክረምት ወቅት ከመሆኑ ጋር በተያያዘ ተማሪዎች የምርጫ ካርድ የሚወስዱት ዩኒቨርስቲያቸው ሆኖ ሳለ ነሀሴ ላይ ወደ ትውልድ ቀያቸው የሚመለሱበት በመሆኑ ሌላ መስተጓጎል የሚፈጥር ሲሆን መምህራንም ቢሆኑ ከሚያስተምሩበት ተቋም ወደ የክረምት ትምህርት መርሀ ግብር የሚከታተሉበት መማሪያ ተቋማት የሚገቡበት ስለሆነ የምርጫ ካርድ ያወጡበት የምርጫ ክልልና ድምጽ የሚሰጡበት ቦታ ፍጹም የማይገናኝ ይሆናል ሲሉ አብራርተዋል፡፡

በሌላ በኩል ምርጫው ፍትሀዊ፣ ነጻና ዴሞክራሲያዊ እንዲሆን ለሁሉም እኩል በወጣ ህግ፣ መመሪያና ደንብ እንዲሁም ፓርቲዎች ከዚህ ቀደም በፈረሙት የቃልኪዳን ሰነድ መገዛት የግድ ነው የሚሉት አቶ ናትናኤል ፓርቲያቸው ለዚህ ዝግጁ መሆኑንና ለአባላቱና ለደጋፊዎቹም ይህንኑ እያስገነዘበ እንደሚገኝ ተናግረዋል፡፡

ባልደራስ ለዕውነተኛ የተሰኘውና በእስክንድር ነጋ የሚመራው የቅድመ ፓርቲ ዕውቅና ያገኘው ድርጅት በበኩሉ በትናንት መግለጫው ምርጫው መቸም ይካሄድ መቼ ለመወዳደር ዝግጁ ነን ብሏል፡፡

ከዚህ የፖለቲካ ፓርቲዎች ሀሳብ ጋር በተያያዘ የምርጫውን መራዘም እየሞገቱ የሚገኙት  በሀገር አቀፍ ደረጃ የሚወዳደሩ የፖለቲካ ድርጅቶች ሲሆኑ በጉዳዩ ዙሪያ ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት ወደ ምርጫ ቦርድ የህዝብ ግንኙነት ወይዘሪት ሶሊያና ሽመልስ ያደረግነው ስልክ ሙከራ አልተሳካም፡፡