አባይ ሚዲያ ዜና -ጥር 15፣2012

ከሳምንታት በፊት በባህርዳር ለዳዕዋ ሲንቀሳቀሱ የነበረው አስር ሙስሊም ወጣቶች መታሰራቸው ይታወሳል፡፡

በመሆኑም የኢትዮጲያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት የቦርድ ጸሐፊ የአቡበክር ሲዲቅ የዳዕዋና ተብሊግ ማዕከል ለዳዕዋ ሲንቀሳቀሱ በዘጌ ተይዘው በባህርዳር ታስረው የነበሩ ወጣቶች እንዲፈቱ የትብብር ደብዳቤ እንዲፅፍ በተጠየቀው መሰረት፥ 10ሩ ወጣቶች እንዲለቀቁ ለአማራ ክልል መጅሊስ፣ የአማራ ክልል መጅሊስ ደግሞ ለክልሉ መንግስት ደብዳቤ በመፃፍ ለመፈታታቸው የየበኩላቸውን አስተዋፅኦ ማድረጋቸው የኮሚቴው አመራር አስነብቧል።