በጋራ ፍርሃት ውስጥ ያለች ሀገር (በሳሙኤል ፍቅረስላሴ ብሩ)

የኢትዮጵያ ቋንቋዎች ጥናት ተቋም ያዘጋጀው የአማርኛ መዝገበ ቃላት ፍርሀትማለት ውስጣዊ ወይም ውጫዊ አደጋ መኖሩን የሚጠቁም ስነ ልቦናዊ ደውል ሲሆንየተደቀነውን አደጋ ለማስወገድ ወይም የሚያስከትለውን ጤት ለመቀነስ አስፈላጊውን እርምጃ እንድንወስድ የሚገፋፋን ስሜትብሎ ይተረጉመዋል ስለዚህ ፍርሀትን አንድ ግለሰብ አደጋ እንዳያግጠመው ቅድመ እርምጃዎችን እንዲወስድ የሚያስጠነቅቅ ስሜት ብለን ጠቅለል ያለ ብያኔ ልንሰጠው እንችላለን በአን የጋራ ፍርሀት ደግሞ አንድ ማህበረሰብ ለፉ ስሜታዊ ልምዶች በተከማቹ የታሪክት ዝታዎች በአስደንጋጭ አሳዛኝ ክስተቶች ምክንያት ተመሳሳይ የፍርሀት ስሜት ውስጥ የሚገባበት በቡድን የተደራጀ እርምጃዎችን እንዲወስድ የሚገፋፋ ማህበራዊ ችግር ነው

ባሳለፍነው የፈረንጆች አመት መገባደጃ ላይ የዓለማቀፍ ክራይሲስ ግሩፕ የተሰኘው እ.ኤ.አ. 2020 . ግጭት እጅግ ገዝፎ ሊታይባቸው ይችላል ያላቸውን አስር ገራት ይፋ ባደረገበት ሪፖርቱ ኢትዮጵ ሦስተኛ ደረጃ ላይ አስቀምጧታልተቋሙ እየተበራከተ የመጣውን የብሔር የሀይማኖት ግጭትን እና ከጥቂት ወራት በኋላ እንደሚከናወን የሚጠበቀው አገራዊ ምርጫ ነኛ ምክንያት ሊሆኑ እንደሚች ስጋቱን ገልጿል

በተመሳሳይ ሂዩማን ራይትስ ዎች ... 2019 ባወጣው ዘገባ ኢትዮጵያ ባለፉት ሁለት አመታት ብሔርና ሀይማኖት ተኮር በሆኑ ጥቃቶች ብቻ ከሁለት ሚሊዮን በላይ የሚሆኑ ዜጎች እንደተፈናቀሉና በመቶዎች የሚቆጠሩ ህይውታቸውን እንዳጡ ይፋ አድ ዘገባው እንደሚያትተው ጥቃቶቹ በመላው የሀገሪቱ ክፍል የተከሰቱ ሆን ጌዲኦ ማህበረሰቦች ሶማሊያ እና ኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት መካከል ተነሳው ግጭት በአስከፊነቱ ገልጾታል ሀተታው ግጭቶቹ የጋራ ገጽታ እንዳላቸው የገለጸ ሲሆን ጥቃቶቹ ናወኑት በቡድን በተደራጁ ወጣቶች ሚሊሻዎች ልዩፖሊስ እና በሠራዊቱ እንደሆነ ገልጿል፡፡

ከዚሁ ጋር በተያያዘ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የሀገር ውስጥም ሆኑ የውጪ ሀገር መገናኛ ብዙሀን ኢትዮጵያውያ በተለያዩ መስኮች እያስመዘገቸው ካሉት ተስ ሰጪ ስኬቶች በተዳኝ ግለሰቦች በቡድን ተደራጅተው በሚያነሷቸው ታሪክ አዘል ፖለቲካ የብሔርና ሀይማኖታዊ ብጥብጦች ምክንያት ዜጎች በጋራ በፍርሀት ውስጥ እንዳሉ ሲዘግቡ ይስተዋላል

ስለዚህ ይህ ጽሁፍ የብሔር እና ሃይማኖታዊ አመፅ ተጋላጭነትን ለመቀነስ ፍላጎት ላላቸው ኢትዮጵያ የሰላም አስተባባሪዎች ቅድሚያ ሊሰቸው የሚገቡ የህዝቡን የጋራፍራቻዎች ለመጠቆምና እነዚህን ችግሮች ለመቅረፍ በሚያደርጉትም እንቅስቃሴ ሊመሷቸው የሚገባቸውን ጥያቄዎች ለመተንተን የታቀደ ነው፡፡

ይህን ጽሁፍ ለማዘጋጀት ያለፉትን ስድስት ወራት ሀገርውስጥና የውጪ ሀገር የኤሌክትሮኒክ ፅሁፎች እናሚዲያዎች ገመገምኩ ሲሆን በነዚህም ዘገባዎች ኢትዮጵያውያን በአምስት ዓይነ የጋራ ፍራቻዎች ውስጥ እንዳሉ ለመረዳት ችያለሁ የብሔርና የሀይማኖት ግጭቶችየክልል ጥያቄ በቅርብ ወራት ውስጥ የሚካሔደው ምርጫና ተከተለውት የሚመጡ ግጭቶች እንዲሁም የአባይ ግድብ ድርድር ዋና ዋና የጋራ ራቻዎች ናቸው ነገር ግን ዚህ ​​ጽሁፍ ውስጥ ብሔርና እና የሃይማኖት ግጭቶች ፍርሃት ላይ ብቻ ትኩረት አደርጋለሁ

ብሔ የሀይማኖት ግጭቶች እና የጋራ ፍርት ኢትዮጵያ

ኢትዮጲያ ከሰማኒያ በላይ የሚጠጉ የተለያዩ ብሄርብሄረሰቦች ቋንቋዎች ተለያዩ ሃይማኖትና ባህል መገኛ መሆኗ ሀገሪቷ የሕዝቦች ሙዚየም የሚል ተቀጽላ እንዲኖራት አድርጓታል ፡፡ በአገሪቱ ውስጥ ይህ ልዩ ልዩ የዘር የሃይማኖት እና የቋንቋ ቡድን ለዘመናት በስምምነት ኖሯል ፡፡

ህዝቡም ቋንቋና ስብጥር አፍሮኤስያዊ እና ናይሎ ሳህራዊ ተብለው በሚጠሩ በሁለት የቋንቋ ክፍሎች ይመደባሉ ፡፡

አፍሮኤስያዊ በሦስት ቡድን ይከፈላልሴማዊ ኩሺቲክ እና ኦሞቲክ ሴማዊው አማራ ትግሬ ጉራጌ አርጎባወዘተ ሲሆን፡፡ ኩሽ ኦሮሚያን ሶማሊያን ቅማንት አላባን አፋርን ሲዳማ ሀዲያን ከምባተን ጌዶን እና የመሳሰሉትን ያጠቃልላል ፡፡ ኦሞአዊ ደግሞ ጋሞ ጎፋዳውሮ ድሜ ሀመር መሎ ከፋ ቃሮ ሸኪቾ ዶርዜላይታ ቁርቴና ችንም በተመሳሳይ ናይሎ ሳህራዊ አኙዋ ኑዌር መዠ በርታ ጉሙዝ ሙርሌ ወዘተ አካቷል

በተማሪም ኢትዮጵያ ከዓለም ታላላ ሀይማኖቶች ጋርም ታሪካዊ ግንኙነት አላት። ክርስትና በአራተኛው ምዕተ-ዓመት የተቀበለች ሲሆን በአፍሪካ የመጀመሪያ ተብሎ የሚታሰበውም የእስላም ሂጅራ ወደ ኢትዮጵያ እንተደረገ የታ ድርሳናት ያትትታሉ እንዲሁም ሀገሪቷ የተለያዩ ሀገርበቀል እምነቶች ያሉባት ስትሆን እስከ 1980 ዎቹ ድረስብዙ ቤተ-እስራኤሎች ኖረውባታል ከዚህ በዘለለ ራስተፈሪ እንቅስቃሴ ኢትዮጵያን ለብዙ አመታ ታላ ክብር እንደሚያያት ይነገራል

ምንም እንኳን በእነዚህ ንቋ የሀይማኖት ክፍሎች የተከፋፈሉ ኢትዮጲያዊያን ተለያዩ ታሪካዊ አመጣጦችና በብዙ ክፍለ ዘመናት ውስጥ ተፈጠሩ በርካታ አንድነትና የልዩነት ጊዜን ቢያልፉም ህዝቦቿ ስፍር ቁጥር በሌላቸው ማህበራዊ ቋንቋ እና ባህ ውህደቶች ለዘመናት አንድነት ኖረዋል፡፡

ይህም ህዝቡ መካከል የቋንቋ የባህል እንዲሁም የሀይማኖት መወራረስን ሲፈጥር ቆይቷል ሰዎች በጋብቻበስራ በተፈጥሮዊና ሰው ሰራሽ ችግሮች ምክንያት ከአንድ ቦታ ወደ ሌላ ቦታ በመሄድ ንብረትን ሲያፈሩ ዘራቸውን ሲተኩ ኖረውል  

ከቅርብ ዓመታት ወዲህ ግን ገሪቱ በአደገኛ ሁኔታ በፍጥነት የጨመረ ባለው የውስጥ ክፍፍል እና ብሔር ተኮር ግጭት እየታመሰች ትገኛለች፡፡

የብሔርና የሀይማኖት ግጭት ምንድን ነው?

የብሔርና የሀይማኖት ግጭት ምንድን ነው? መነሻውስ? ግጭቱ እንዴት ይፈታል? ወዘተ ለሚሉ ጥያቄዎች ቀጥተኛና ወጥ መልስ መስጠት ቢያዳግትም በተለያዩ የግጭት መስኮች ጥናት የሰሩ ምሁራንን አጣቅሶ ስለ ጉዳዩ ማብራርያ መስጠት ግን ይቻላል፡፡

ስለዚህ ኢትዮጲያን የብሔርና ሀይማኖት ተኮር ግጭት መነሻና አሁን ያለበትን ደረጃ ከማብራራቴ በፊት በተለያዩ የጥናት መስኮች ምርምር ያካሄዱ ምሁራን ከራሳቸው የምርምር ውጤት በመነሳት ግጭትን ረጎሙበትን ንገድ ማስቀደሙ የተሻለ ሆኖ አግኝቼዋሁ፡፡

አንዳንድ ምሁራን ግጭትን ከፍላጐት አለመሳካትና ከአቅርቦት እጥረት ጋር ያያይዙታል፡፡ አሌክሳንደር ሽሚድ የተባሉ የማህራዊ ንስ ምሁር ግጭት ከፍ ያለ ቦታ ወይንም ደረጃ ለማግኘት በሚረግ ጥረትና በሀብት ንነት የሚከሰት አለመግባባት ነው፡፡ ሲሉ ሬሞንድ ፊሸር በበኩላቸው ግጭት ግንኙነት ባላቸው ሁለት ወይም ከዚያ በላይ በሆኑ ቡድኖች መካከል በሚኖር የዓላማ ልዩነት አንዱ የሌላኛው የበላይ ለመሆን ሲሻ የሚፈጠር ተቃርኗዊ ስሜትነው በማለት ይበይኑታ፡፡

ዶች እና ኮልማን የተባሉ የማህበራዊ ግጭቶች አፈታት ምሁራን ደግሞ ከላይ ሽሚድና ፊሽ ከተሰጠውና የግጭት መንስኤ ላይ ካተኮረው ብያኔ ወጣ ብለው ውጤቱ የሚያትት ገለፃ ይሰጣሉ፡፡ ግጭትን የምንቆጣጠርበት ወይንም የምንፈታበት መንገድ ውጤቱን ገንቢ ወይንም አፍራሽ እንዲኖረው ያደርጋል፡፡ ብለው ያስቀምጣሉ

ይህ በዶች እና ኮልማን, ተሰጠው ትርጉም ግጭት በሰው ልጅ መካከል በሚፈጠር ማህበራዊ ግንኙነት መከሰቱ አይቀሬቢሆንም ወደ አንዳች መልካም ግብ ማምጣት እንደሚቻልም ያመከተ ነው፡፡

 ምንም እንኳን ግጭት አሉታዊ ጎኑ የበዛ ቢሆንም ከላይ የጠቀስናቸው ምሁራንግጭት ማንነትን ለመገንባትና ራስንሆኖ ለመገኘት አስተዋፅኦ የጎላ እንደሆነና ሰዎች ህብረትን እንዲፈጥሩ በጠላትነት የሚተያዩ ቡድኖችን ወይንም ግለሰቦችን ወደ አንድ የጋራ ግብ እንዲመጡና ግባቸውን እንዲያሳኩ በማድረግ በመካከላቸው የተፈጠረውን ስጋት ለመፍታት ያስችላል ብለው ይተነትናሉ ይሁን እንጂ ግጭትን የምንፈታበትና የምንቆጣጠርበት ዘዴ ጎጂና ጠቃሚነቱን ይወስናል የሚለው ሀሳብ ተገቢነት ሚዛን ይደፋል፡፡

የብዙ ግጭቶች መነሻ ምክንያት በትክክል ይሄ ነው ብሎ መናገር አስቸጋሪ ነው ምክንያቱም ብዙ ጊዜ ግጭቶች በአንድ ጊዜ በሚፈጠር ሁነት ብቻ የሚመጡ ሳይሆኑ የበርካታ ችግሮች ድምር ውጤት በመሆናቸው ነው፡፡ በአንድ ቡድን ወይም ማህበረሰብ ውስጥ ያለ የሀሳብና የፍላጐት ተቃርኖ ድንገት ምክንያት ሲያገኝ ፈንድቶ በመውጣት ሁለቱን አካላት ወደ ከባድ ግጭት እንዲያመሩ ምክንያት ይሆናል

ዳንኤል ካትዝ የተባሉት የአእምሮ ጥናት ተመራማሪ ‹‹የብሔራዊ ስሜት እና የአለም አቀፍ የግጭት አፈታትስልቶች›› በሚለው መጽሀፋቸው ከላይ ጠቀስኩትንምክንያት ከግምት ውስጥ በማስገባት ግጭቶች በሶስት ዋናዋና ምክንያቶች ማለትም በኢኮኖሚ በእሴት እና በስልጣን እንደሚከሰቱ ይገልፃሉ
በአን የብሔርና ሀይማኖት ተኮር ግጭት የምንለው ደግሞ በሁለት ወይም ከዚያ በላይ በሆኑ ተቀናቃኝ ጎሳዎችየሀይማኖት ተከታዬች ወይም ቡድኖች መካከል የሚደረግ ግጭት ነው ነገር ግጭቱ መነሻ ፖለቲካ ማህበራዊ ኢኮኖሚያዊ ወይም ሃይማኖታዊ ሲሆን በግጭት ውስጥ ያሉ ግለሰቦች ኅብረተሰባቸው ወይም ለቡድናቸው ህልውና ሀይልን በመጠቀም የሚያደርጉት ምናልባትም በጣም አስከፊሆነ ጦርነት ወይም ብጥብጥ የሚያስነሳ ማህበራዊ ቀውስ ማለት ነው

በኢትዮጵያ ውስጥ የብሔርና ሀይማኖት ተኮር ግጭት የሚለው ቃል የእለት እለት የመገናኛ ብዙሀን ትወራዊ ቅኝት ከሆነ ሰነባብቷል

በሚሊዮን የሚቆጠሩ ዜጎች በጎሳበሀይማኖትና በክልል ግጭት የተነሳ ከኖሩበት ቀዪ ሲፈናቀሉ ሲገደሉየሃይማኖት ስፍራዎች ሲቃጠሉ መስማት ማየት አስደንጋጭ ዜና መሆኑ ቀርቷልወጣቶች የጥቂት እራስወዳድ ግለሰቦች የፖለቲካ ጀንዳ መሳሪያ መሆናቸውም እየተበራከተ መጥቷል፡፡

በአጠቃላይ በአሁኑ ወቅት በኢትዮጵያ ያሉ የብሔርና ሀይማኖት ተኮር ግጭቶች በገጠር እና በከተማ ውስ ያሉ ዜጎችን በጋራ ፍርሀት ውስጥ እንደከተቱ ለማወቅ በቅርብ ጊዜ ውስጥ አየታተሙ የሚወጡ የግልም ሆኑ የመንግስት ጹሁፎች ዘገባዎች አየነተኛ ማስረጃዎቻችን ናቸው፡፡

እነዚህ በየጊዜው መልካቸውን እየቀያየሩ የሚከሰቱ ግጭቶች መጠነ ሰፊ የማሻሻያ እርምጃዎችን በመውሰድ አምባገነን የነበረውን የመንግስት መዋቅር መቀየር በመሞከርኢትዮጵያ በአካባቢው ከሚገኙ ገራት ጋር የነበራትን ግንኙነት በማሻሻ ከፍተኛ አለም አቀፍ እውቅና ሯቸ ጠቅላይ ሚኒስተር አብይ አህመድ ዋና ተግዳሮት ነው ሰንብተዋ

ለዚህም እንደምክንያት የሚጠቀሰው ጠቅላይ ሚኒስተሩ እስካሁን የወሰዱ የለውጥ እርምጃዎች ታሪካዊ የሆኑና ከባለፈው መንግስት አንስተው ሲነሱ የነበሩ በክልሎች መካከል ያሉ የድንበር ጥያቄዎች ርን መሰረት አድርጎ በሚፈጸሙ ጥቃቶች የክልሎች የፖለቲካ ውክልና እና የህገመንግስት ጥያቄን ለመመለስ በቂ አለመሆኑ ነው  

ይህም የፖለቲካ ምህዳሩን መስፋት ተጠቅመው ለተፈሩ በዘር ላይ የተመሰረቱ የፖለቲካ ድርጅቶች በጥያቄ ውስጥ ያለውን ህዝብ ወደ ፈልጉት አቅጣጫ ለመምራት መንገድ ከፍቶላችዋል በዚህም ብዙ የፓለቲካ ተንታኞች እስካሁን በሀገሪቷ በተፈጠረው የጸጥታ ቀውስ በአንድም ቢሆን በሌላ መልኩ የነዚህ ድርጅቶች ተሳትፎ እንዳለበት ይናገራሉ

በተጨማሪም ጵያ ዘጠኙን ክልላዊ መንግሥቶች ስትመሠርት የተጠቀመችው የአንድ ብሔር የበላይነት አለበት ተብሎ ሲተች የነበረው የብሔር ፌደራሊዝም ሥርዓት ለብሔርተኝነት መንሰራፋት እና በብሔሮች መካከል ግጭት ለመቀስቀስ ዋነኛ መንስኤ እንደሆነ ብዙዎች ይስማሙበታ

ከህገ-መንግስቱም ተጓዳኝ በተለያየ ጊዜያት በመንግስትም ሆነ በግለሰቦች ሲጠቀስ የነበረው ማህበራዊ ሚዲያዎች የሚሰራጩ የሐሰት ዜና የጥላቻ ንግግሮች ሌላኛው ምክንያት ተደርገው ሊወሰዱ ይችላሉ፡፡

ምንም እንኳን ሀገሪቷ በእንደዚህ ባለ አጣብቂኝ ውስጥ ብትሆንም በስልጣን ላይ ያለው መንግስት ችግሮቹን ለመፍታት ምንም አይነት ሙከራ አላደረገም ለማለት አልደፍርም

መንግስት ሮቹን ይፈታሉ ያላቸውን የብሄራዊ እርቅና ሰላም እንዲሁም የአስተዳደርና ድንበር ኮሚሽኖችና የመሳሰሉትን ኮሚቴዎች ማቋቋ የሚታወቅ ነውነገር ግን እነዚህ ኮሚቴዎች ችግሮችን ከስር መሰረታቸው ለመፍታት ሁሉን አካታች የሆነ ሃገር በቀል እውነተኛ እርቅ በማህበረሰብ መሃካል እንዲፈጠር መስራት ይኖርባቸውል

እንዲሁም ሁሉም ዜጋ በሰከነ መንፈስና በሰለጠነ መንገድ የራሱን ሀላፊነት መወጣት እንዳለበት አምናለውስለዚህ እኔም ይህን ጽሁፍ ከመዝጋቴ በፊት ለጹሁ ዋነኛ ትኩረት የሆነው በኢትዮጵያ የሰላም አስተባባሪዎች በተለየም ከጥቂት ወራት በኋላ እንደሚከናወን የሚጠበቀው አገራዊ ምርጫ ጋር በተያያ ቅድሚያ ሰጥተው ጥናታዊ መልስ ሊፈልጉላቸው ይገባል የምላቸውን ጥያቄዎች አጫጭር የመፍትሄ ሃሳቦችን በቅደም ተከተል አስቀምጣለሁ

1. በተቃረኑት የብሄር ወይም የሃይማኖት ቡድኖች መካከል የተፈጠረው ጠላትነት የቅርብ ጊዜ ሂደት ነው ወይንስ ረጅም ጥላቻ እና ታሪካዊ ቁርሾ ያዘለ ነው? ወይስ በፖለቲካ በኢኮኖሚያዊ ለውጥ ምክንያት አዳዲስ የዘመናዊ ጥላቻ ዓይነቶች ብቅ ማለት ተከትሎ የተፈጠሩ ቁርሾዎች ናቸው?

ይህን ጥያቄ በመመለስ ለተፈጠሩት ተቃርኖዎች ዘመናዊ ወይም ሀገር በቀል የእርቅ መፈትሄዎችን ማፈላልግእንዲሁም መንግስት ወይም ሃይማኖታዊ ግጭቶችውስጥ ገለልተኛ በመሆን በቀደሙት መንግስታትና ማህበረሰብ ተበደልን ያሉ ቡድኖች ታሪካዊ ኢፍትሃዊነትን መመርመርና የጋራ ታሪኮችን መፍጠር የሚቻልበትን መዋቅርመዘርጋት

2. . ትኞቹ ፖለቲካ ልሂቃን ወይም ሚዲያ አካላት የጎሳ ማንነቶችን ለመገንባት ወይም የፖለቲካ እሳቤዎችን በመጠቀምምናባዊ ማህበረሰቦችንጠር የሌሎች ብሄረሰቦች ወይም ሀይማኖት ተከታዬችን ምስል በጠላትነት የመረቅጽ ኃይል አላቸው?

እነዚህን ቡድኖች ማወቅ ከተቻለ በምን መልኩ መደራደርና ሚዛናዊ የሆነ የመግባቢያ ሰነድ ማዘጋጀት እንደሚቻል ማሰብነገር ግን ለመደራደርና ወደ እርቅ መምጣት በማይፈልጉት ቡድኖች ላይ ተገቢ እርምጃ በመውሰድ የዚጎችን ደህንነት ማስጠበቅ

3. . የፖለቲካ ልሂቃን ወይም የምርጫ ተወዳዳሪዎች የብሔርና የሀይማኖት ግጭቶችን የታሪክ ቁርዎችን በምን መልኩ እንደ ማጣቀሻ እየተጠቀሙ የምርጫ ቅስቀሳቸውንና የአባላት ምልመላቸውን እያካሄዱ ይገኛሉ?

ይህ ጥያቄ ታሪክን ለግል ጥቅም በማዋል በህዝቦች መካከልልዩነትን በሚፈጥሩ ግለሰቦች ላይ ፍትሀዊ እርምጃ ለመውሰድና መራጩ ህዝብ በሀሰት መረጃና ታሪክ ተታሎ በአግባቡ ሊወክለው የማይችለውን ሰው እንዳይመርጥ ይረዳል

4. . የቋንቋየሀይማኖት የትምህርት ፖሊሲው እንዲሁም ሕገመንግስቱ የተፈጠሩ ላሉ ግጭቶች ምንሚና ይጫወታሉ?

ህገመንግስቱም ሆነ ሌሎች ፓሊሲዎች ግጭት የመፈጠር ሀይል አላቸው ተብሎ ከታመነህዝብ የተመረጠ ዜጎችን ጋራና በመተሳሰብ ተከባብሮርና ተስማምቶ ሊያኖር የሚያስችል በሀገሪቷ ወግና ስርአት የተቃኘ ህገ-መንግስት ማዋቀር በተጨማሪም በባህል በቋንቋና በአስተሳሰብ ላይጋሬጣ የሚሆኑ የውጪ ተፅእኖችን መርህ ማበጀት

5. . የብሄር ወይም ሃይማኖት ግጭቶች በስተጀርባ ያሉ ውጪ ሀገራት ተጽእኖና የዲያስፖራ ቡድኖች ሚና ምንይመስላል?  

እነዚህ አካላት በምን መነሾ ተስበው ጭቶችን እንደሚያነሳሱና በምን መልኩ ድጋፍ እንደሚሰጡ ማጥናትበዚህም በአገሪቱ ውስጥ ውጥረትን በመስቀስቀስና ግጭትን በማስፋፋት የሚታወቁ የዲያስፖራ ቡድኖችየውጪ ድጋፍ ሰጪ አካላት አደብ ሊያስገዛ የሚችል አጥርማበጀት

6. . በሀሪቱ ውስጥ በውጪ ያሉ የመገናኛ ብዙሃንና የማህበራዊ ሚድያዎች በብሔርና የሀይማኖት ተኮር ግጭቶች ላይ ያላቸው ሚና ምን ያህል ነው?

ይህንን ዘመናዊ ችግር ለመመርመር ሁለት ንዑስ ጥያቄዎችን ማንሳት ያስፈልጋልየመገናኛ ብዙሃንና የማህበራዊ ሚድያዎች የግጭቶች አዘጋገብና የመረጃ አሰባሰብ መብትና ግዴታ በህገመንግስቱ ውስጥ እስከምን ድረስ ይሄዳል? ሁለት እነዚህ ሚዲያዎች በምን መልኩ ያለፉ የግጭት ታሪኮችን ማስታወስና የትኞቹን የታሪክ ማጣቀሻዎች መጠቀም ይችላሉ? የሚሉ ናቸው

7. . በመጨረሻም ሀገራዊ ትውስታዋቻችን ለምሳሌ የታሪክመዛግብትሀውልቶችንና አፈታሪኮቻችንን በጥናት በመደገፍ በህዝቦች መካከል መከፋፈልና ጥላቻን ንደማያመጡ ማረጋገጥ ናቸው