አባይ ሚዲያ ዜና ጥር 20፣2012

በዛሬው እለት ማለትም ጥር 20 ቀን 2012 ዓ.ም ከንጋቱ ጀምሮ የተደራጁ ወጣቶች ከሀረር ወደ ጅጅጋ፣ድሬድዋና ሌሎች አካባቢዎች የሚወስዱ መንገዶችን እንዲሁም የሀረር ከተማ የውስጥ ለውጥ መንገድን ጎማ በማቃጠል ዘግተው አርፍደዋል።

በተጨማሪም ባንኮች፣ ትምህርት ቤቶች፣ የመንግስት መስሪያ ቤቶችና የግለሰብ ሱቆች ሳይቀሩ በግዳጅ እንዲዘጉ ተደርጓል።

በደረሰን መረጃ መሰረትም የፀጥታ አካላት ያደረጉትን እንቅስቃሴ ተከትሎ የሀረር የውስጥ ለውስጥ መንገድ እንዲከፈት የተደረገ ቢሆንም ከሀረር ከተማ ወደ ውጭ የሚወስዱ መንገዶች ግን ይህ ዜና እስከተጠናቀረበት ድረስ አለመከፈቱንና አስፈሪ ድባብ መኖሩን ሰምተናል፡፡

በጉዳዩ ላይ የከተማውን ነዋሪዎች ለማነጋገር ያደረግነው ጥረት ለጊዜው አልተሳካም፡፡