አባይ ሚዲያ ጥር 28፤2012

 

በኮሮናቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር ከ20 ሺህ በላይ መሆን በተማሪዎች ዘንድ ከፍተኛ ስጋትን ፈጥሯል ምንም እስካሁን በቫይረሱ የተያዙ ኢትዮጵያውያን ባይኖሩም፤ ወደ አገራችን መልሱን በሚሉ በሺዎች በሚቆጠሩ አፍሪካውያን ተማሪዎች ተሞልታለች።

ከሰው ጋር ንክኪ በሚያስፈራበት ዘመን፤ የኢትዮጵያውን ተማሪዎችም በዚሁ ግራ መጋባት ውስጥ ናቸውበዉሃን ዩኒቨርስቲ ከሦስት መቶ በላይ ኢትዮጵያውያን ተማሪዎች ያሉ ሲሆን፤ በሁቤይ ግዛት ውስጥ በሚገኙ ከተሞችም ያሉ ኢትዮጵያውያን ጨምሮ በአጠቃላይ ከ400 በላይ የሚሆኑ ተማሪዎች አሉ።

በዉሃንም ሆነ በአካባቢው የሚገኙ ተማሪዎች እንቅስቃሴ የተገደበ ስለሆነ ብቸኛው የመገናኛ መንገዳቸውም በኢንተርኔት መልዕክት በመላላክ ነው ሶሊያና ከተማሪዎች ማደሪያ ውጭ ተከራይታ በራሷ ስለምትኖር ሁኔታዎችን ቀለል ቢያደርግላትም በተለያዩ ዩኒቨርስቲዎች ውስጥ የሚያድሩ ተማሪዎች ምግብ፣ ውሃም ሆነ ሌሎች ቁሳቁሶች ቢቀርብላቸውም አንዳንዶች ቸልተኝነት እንዳለባቸው ከኢትዮጵያውያኑ ሰምታለች።

ተማሪዎቹ የቡድን ቻት ስላላቸው ያሉበትን ሁኔታ፣ ስጋታቸውን እንዲሁም ሌሎች ጉዳዮችን ይቀያየራሉ”አንዳንድ ተማሪዎች ጥሩ ሁኔታ ላይ እንዳልሆኑ ይናገራሉ። ትምህርት ቤቱ ቸልተኝነት በማሳየቱ ወይም የሚገባቸውንና የሚያስፈልጋቸውን ባለመስጠቱ ይሆናል” ትላለች ምንም እንኳን በሁቤይ ግዛት ሁሉም ሰው እንቅስቃሴውን እንዲያቋርጥና፣ በቤቱ እንዲገደብ ቢወሰንም የቻይና መንግሥትም ማንኛውንም እርዳታ ለመለገስ መዋቅር ተዘርግቷል።

ተማሪዎቹ በተደጋጋሚ መልስ ይሰጠን እያሉ እየጠየቁ ሲሆን ማህበሩም “ታገሱን ዝግጀት ይፈልጋል። ኤምባሲውም የራሱ የሆነ ሂደት አለው፤ የውጭ ጉዳይም እንዲሁ፤ ይህንን ሂደት እየተጠባበቅን ነው ያለነው” የሚል ምላሽም በመስጠት ላይ ናቸው።

ሆነም ቀረም “ኢትዮጵያ ውስጥ ያሉ ቤተሰቦች በጣም አስከፊ ሁኔታ ውስጥ እንዳለን እያሰቡ እንዲጨነቁ አልፈልግም፤ ከራሳቸው ዜጋ ባልተናነሰ መልኩ ክትትል እየተደረገልን ነው” በማለት ቤተሰቦች መረጋጋት አለባቸው ትላለች ሶሊያና።

ሁሉም ሰው በጭንቀት ላይ እንደሆነ የምትናገረው ሶሊያና “ምክንያቱም መልስ እየጠበቅን ነው፤ ለምንም ነገር መዘጋጀት አለብን፤ እሱ ላይ ትንሽ ግራ ስለተጋባን፤ አብዛኞቻችን መወዛገብ ሁኔታ ላይ ነን” ትላለች ሲል የዘገበው ቢቢሲ ነው፡፡