አባይ ሚዲያ ጥር 30፤2012

 

የኤርትራው ፕረዝደንት ኢሳይያስ አፈወርቂ በትላንትናው ዕለት ለኤርትራ ቲቪ ጋዜጠኞች መግለጫ ሰጥተዋል የምስራቅ አፍሪቃን ወቅታዊ የፖለቲካ ሁኔታ በተለይም የኢትዮ~ኤርትራን ግንኙነት ምን እንደሚመስል በጋዜጠኞች የተጠየቁት ፕሬዝደንቱ በኢትዮጵያና ኤርትራ መካከል በአንድ ዓመት ተኩል ውስጥ ብዙ ስራ ተሰርቷል ማለት ባይቻልም መልካምነቱን ግን ይጎለብታል ሲሉ ገልጸዋል።

በኢትዮጵያና ኤርትራ መካከል ጸብና መቃቃር ፈጥረው እናተርፋለን የሚሉ ህወሓትና ሌሎች የውጭ ሃይሎች መኖራቸው የቀጠናው ግንኙነት እንዳይጎለብት ቢያደርገዉም ለተሻለ ለውጥ እየሰራንበት እንገኛለን ሲሉም ፕረዝደንቱ አብራርተዋል ፕረዝደንት ኢሳይያስ ኢትዮጵያና ኤርትራ ላለፉት 80 ዓመታት ባጠቃላይ ላለፉት 20 ዓመታት ደግሞ በተለይም ቀጠናውን ለማዳከምና አትራፊ ለመሆን ብዙ የውጭ ሃይሎች ቢጠቀሙበትም አሁን ላይ ግን ይህ አይሰራም ሲሉ ገልጸዋል።

የኢትዮጵያ የውስጥ የብሄር ጥላቻ ያሳሰባቸው ፕረዝደንት ኢሳይያስ ጥልን መኮስኮስ ቀላል ቢሆንም ፍቅርን መገንባት ግን ከባድ ነው ብለዋል ይህ ወቅታዊ የኢትዮጵያ የህዝብ ለህዝብ ግጭትም የዚህ ማሳያ ነው ሲሉም ገልጸዋል የኢትዮጵያ የእርስ በርስ ግጭት ለአገሪቱ ብቻ ሳይሆን ለቀጠናው አሳሳቢ እንደሆነ ገልጸው ፕሬዝደንቱ ሁላችንም ትኩረት ሰጥተን ተባብረን ማስተካከል አለብን ሲሉ ይመክራሉ አያይዘውም ምንም እንኳን የኢትዮ~ኤርትራ ጦርነት መንስኤ ባድመ እንደ ምክንያት ቢጠቀስም እውነቱ ግን እሱ እንዳልነበር  ገልጸዋል ህወሓት በኤርትራ መንግስትና በዐቢይ የለውጥ መንግስት ተከበናል ሊወጉን ነው ተነሱ ታጠቁ ማለታቸው አዲስ ባይሆንም ባድመ ላይ እያደረጉት ያሉት የሰፈራ ፕሮግራምና የመሳሰሉት እንቅስቃሴዎች ግን እንዳልወደዱት ፕረዝደንቱ ያብራራሉ።

ኤርትራ ምንም እንኳን የአልጀርስ ስምምነት ይጽናልኝ ባትልም ህወሓቶች ግን በተቃራኒው በዚህ  ህዝብን እያነሳሱ ነው ሲሉ ኮንነዋልይህ በእንዲህ እያለ ኢትዮጵያ ላለፉት 30 ዓመታት ሰዋዊ የአስተሳሰብ ለውጥ ላይ ባለመስራቷና በብሄር መከፋፈሏ አሁን ላለውከባድ ግጭት ቢዳርጋትም ዶ/ር ዐቢይ ከባድ ውሳኔ መወሰን ይጠበቅባቸዋል ብለዋል ፕረዝደንት ኢሳይያስ::