አባይ ሚዲያ የካቲት 01፤2012

በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ከደብረ ብርሀን ወደ ዓለም ከተማ የሚወስደው መንገድ በአካባቢው ወጣቶች መዘጋቱ ተገለጸ መንገዱ በመዘጋቱ ምክንያትም ወደ መርሀቤቴ፣ ሚዳ ወረሞ እና እንሳሮ ወረዳዎች የሚሄዱ መንገደኞች መቸገራቸውን ለኢትዮ ኤፍ ኤም ተናግረዋል።

እንደ የአይን እማኞቹ አስተያየት ከሆነ መንገዱ የተዘጋው መንገዱ ወደ አስፓልት ይቀየርልን ብለን ለመንግስት ብናመለክትም የሚሰማን አጣን በሚል ምክንያት ወጣቶቹ እንደዘጉት ተናግረዋል በተለይም ህጻናት የያዙ ወላጆች ምግብና ውሀ በማጣታቸው ለእንግልት ተዳርገናል የሚመለከተው የመንግስት አካል መንገዱን በአፋጣኝ ያስከፍትልን ሲሉ ጠይቀዋል።