አባይ ሚዲያ የካቲት 02፤2012

የጋምቤላ ክልል መስተዳድር ጽህፈት ቤት በሙቀት ምክንያት ከየካቲት 1 ቀን 2012 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ሚያዝያ 30 ቀን 2012 ዓ.ም ድረስ ለሶሰት ወራት ያክል የስራ ሰዓት ለውጥ ማድረጉን አስታውቋል።

በዚህም መሰረት ጧት የስራ ሰዓት መግቢያ 1 ሰዓት ሲሆን መውጫ 5 :30 እንዲሁም ከሰዓት የስራ ሰዓት መግቢያ 10 ሰዓት ሲሆን መውጫ ደግሞ 12 :30 እንደሆነ ተገልጿል።

በአካባቢው ከፍተኛ የሙቀት መጠን መፈጠሩ የስራ ሰዓት ለውጥ እንዲደረግ ምክንያት መሆኑን ክልሉ አስታውቋል።