አባይ ሚዲያ የካቲት 02፤2012

በድሬዳዋ ከተማ አስተዳድር፤ ሚሊንየም መናፈሻ ውስጥ በተፈጠረ አለመግባባት አንገቱ ላይ በስለት ተወግቶ የ17 ዓመት ወጣት ትናንት የካቲት 1 ቀን 2012 ዓ.ም. አመሻሽ ላይ ተገድሏል።

ወጣቱ ከወንድሙና ከእህቱ ጋር በመናፈሻ ቦታው እየተዝናና እንደነበር የአካባቢው ምንጮች መግለጻቸውን ኢትዮጲስ ዘግባለች ።

አቶ ቢንያም ታደሰ የተባሉ የአይን እማኝ በተለይ ለኢትዮጲስ እንደገለፁት አለመግባባቱ የተፈጠረው በሟችና በሚሊኒየም መናፈሻ አስተናጋጆች መካከል ሲሆን የልዩነቱ መንስዔ ደንበኞች ከተገለገሉበት አጠቃላይ ገንዘብ ውስጥ የ65 ብር አለመተማመን መፈጠሩ ነው።

በአሁኑ ጊዜ በወጣቱ ግድያ የተጠረጠሩ አምስት አስተናጋጆች በቁጥጥር ሥር ውለው ምርመራ እየተደረገ መሆኑ ታውቋል ።