አባይ ሚዲያ የካቲት 02፤2012

ኢትዮጵያ የራሷን የነዳጅ ምርት ለአገር ውስጥ ፍጆታ መጠቀም የጀመረች ሲሆን፤ የማዕድንና ነዳጅ ሚኒስቴር ባለፉት 6 ወራት 1650 በርሜል ድፍድፍ ነዳጅ ለሀገር ውስጥ ገበያ መቅረቡን አስታውቋል፡፡

‹‹ኒው ቢዝነስ ኢትዮጵያ›› የተሰኘው ድረ ገጽ፣ ማዕድንና ነዳጅ ሚኒስቴርን ጠቅሶ ባወጣው መረጃ፤ በሙከራ ደረጃ ካለፈው ሐምሌ 2011 ጀምሮ ላለፉት 6 ወራት 1650 በርሜል ድፍድፍ ነዳጅ ለሀገር ውስጥ ገበያ መቅረቡንና በዚህም ሀገሪቱ ከውጭ ተገዝቶ ለሚገባ ነዳጅ ታወጣ ከነበረው የውጭ ምንዛሪ፣ 55ሺህ 994 ዶላር ማዳን መቻሏን ጠቁሟል፡፡

በኦጋዴን ያለውን የነዳጅ ምርት ከሀገር ውስጥ ገበያ ባሻገር ወደ ውጪ ለመላክ፣ ከኦጋዴን እስከ ጅቡቲ የውስጥ ለውስጥ ነዳጅ ማስተላለፊያ መስመር ግንባታ በቅርቡ እንደሚጀመርም ታውቋል፡፡