አባይ ሚዲያ የካቲት 02፤2012

የኮሮና ቫይረስ በቻይና መከሰቱን ተከትሎ ብዙዎች ወደ ኢትዮጵያ እንዳይገባ ስጋት ውስጥ ናቸው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ደግሞ ወደ ቻይና ከተሞች በረራውን መቀጠሉ ለብዙዎች ስጋት ዋነኛው ምክንያት ነው።

ኢትዮ ኤፍ ኤም ከኢትዮጵያ አየር መንገድ አቭዬሽን አካዳሚ ስራ አስኪያጅ አቶ ሰለሞን ደበበ ጋር በጉዳዩ ዙሪያ ቃለ መጠይቅ አድርጓል ምላሽ ተቀብሏል አቶ ሰለሞን ደበበ የኢትዮጵያ አየር መንገድ በቻይና ወደ 5 ከተሞች በሳምንት 35 በረራዎችን እንደሚያደርግ ገልጸው ከቫይረሱ ጋር በተያያዘ ሳይሆን ከቻይና አዲስ ዓመት ጋር በተያያዘ የበረራ ማሻሻያዎች ተደርገዋል ብለዋል፡፡

የኢትዮጵያ አየር መንገድ የቫይረሱ በተስፋፋባት በሁቤ ግዛት ከዚህ ቀደምም አይበርም አሁንም አይበርም ያሉት አቶ ሰለሞን የኮረና ቫይረስን አስመልክቶ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ለምን በረራ አያቆምም የሚለው ጥያቄ ልክ ቢሆንም በረራ ማቆም ግን ለዚህ ችግር መፍትሔ ነው አይደለም የሚለውን በትክክለኛ አተያይ መመልከት እንደሚያስፈልግ ይጠቁማሉ፡፡

ለዚህ የቫይረስ ስጋት የኢትዮጵያ አየር መንገድ በመብረሩ ነው ወይ ለሚለው አይደለም ነው መልሱ እንደውም የኢትዮጵያ አየር መንገድ በቀጥታ እየበረረ ከሌሎቹ የቻይና ግዛቶች የሚነሱት መንገደኞች አስፈላጊው ምርመራ መደረጉን የማረጋገጥ እድል አለው ሲሉም አክለዋል፡፡

ባለመብረሩ ደግሞ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ወደ ኢትዮጵያ መምጣታቸው አይቀርም የሚሉት ስራ አስኪያጁ ለምን ቢባል ሌሎች አየር መንገዶች ወደ ቻይና የሚበሩ በመሆናቸው ነው ሲሉ ያስረዳሉ በረራን ላለማቋረጥ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከቻይና ጋር የገባው ግዴታ የለም ሲሉ የሚገልጹት ሃላፊው አየር መንገዱ ከሚበርባቸው ሀገሮች ጋር ጠንካራ ግንኙነት አለው በመጥፎም በመልካም ጊዜያቶች ፤ ከዚህ አንፃር አየር መንገዱ እንደዚህ አይነት መልካም ያልሆኑ ችግሮች ሲፈጠር እርምጃ ለመውሰድ አይቸኩልም ብለዋል ታሪካዊ ልምዳችንም የሚሳየው ይህንን ነው፡፡ ከዚህ ቀደም ኢቦላ ቫይረስ በተከሰተ ጊዜ ፤ አዲስ ኤርፖርት በሚሰሩበትና ከተማቸውን በሚቀይሩበት ጊዜ የኢትዮጵያ አየር መንገድ በጋራ ዘልቋል፡፡ ይህ ደግሞ የተለየ ስምምነት ኖሮ ሳይሆን ያ ባህል ስላለን ነው ሲሉም አቶ ሰለሞን አብራርተዋል፡፡