አባይ ሚዲያ የካቲት 02፤2012

የአዲስ አበባ ቀላል ባቡር ትንስፖርት አገልግሎት ከሀምሌ እስከ ታህሳስ ባሉት ስድስት ወራት ጊዜ ውስጥ በአምስት ባቡር ላይ በደረሰ የመኪና ግጭት እና በአጥር ላይ በደረሰ 36 አደጋ 96 ሺህ 250 ብር፤ እንዲሁም በኬብል ስርቆት ስልሳ ሺህ ብር የሚገመት ጉዳት እንዳጋጠመው አስታወቀ።

አገልግሎቱ እንደገለጸው በማቋረጫዎች ላይ መኪና ከባቡር ጋር የመጋጨት አምስት አደጋዎች ተከስተዋል።

በመሰረተ ልማት ላይ እና በአጥር ላይ ደግሞ 36 የመኪና አደጋ ተፈጥሯል። የደረሱት አደጋዎች በአማካይ 96 ሺህ 250 ብር ይገመታሉ።

አብዛኛው የኬብል ስርቆት የሚፈፀመው በእስጢፋኖስ፤ በስታዲየምና በልደታ ጣቢያዎች አካባቢ ሲሆን፤ የተወሰደው ኬብል 60 ሺህ ብር የሚገመት ነው።