አባይ ሚዲያ የካቲት 02፤2012

በደቡብ ጎንደር አስተዳደር ዞን ፎገራ ወረዳ አባኪሮስ ቀበሌ ነዋሪ የሆኑት ቄስ ጌቴ ጥበቡና ወ/ሮ የማታ ዋሴ በደምቢ ዶሎ ዩኒቨርሲቲ በነበረው ሁከት ወደ ቤተሰቦቻቸው በመመለስ ላይ ሳሉ ባልታወቁ ግለሰቦች ከታገቱ ተማሪዎች መካከል የሆነችው የ21 ዓመቷ ወጣት ስርጉት ጌቴ ቤተሰቦች ናቸው፡፡

ተማሪዋ በማይታወቁ ግለሰቦች መታገቷን ለአጎቷ ልጅ በስልክ እንደነገረችውና ከአባቷ ጋርም  በስልክ 3 ጊዜ የተገናኙ ሲሆን የመጨረሻ የሥልክ ንግግራቸውም ታህሳስ 8/2012 ዓ/ም መሆኑን ቄስ ጌቴ ገልጸዋል ፡፡

በድህነት አቅም ተቸግረው ያስተማሯት ልጃቸው መንግስት ባለበት ሃገር እንደዚህ እንደወጣች መቅረቷ እንዳሳሰባቸው ወ/ሮ የማታ በመግለፅ መንግስት የታገቱ ልጆቻቸውን በአስቸኳይ እንዲያስመልስላቸው አሳስበዋል ፡፡

መንግስት በደምቢ ዶሎ አካባቢ ታግተው የሚገኙ ልጆችን እንዲያስለቅቅ የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች እንቅስቃሴ ቢያደርጉም ውዥንብር የሚፈጥሩ መረጃዎች ከመውጣታቸው ሌላ ጉዳዩ እስካሁንም መቋጫ አላገኘም፡፡