አባይ ሚዲያ የካቲት 03፤2012

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ምልዐተ ጉባኤ በወቅታዊ የቤተ ክርስቲያኒቱ ጉዳዮች ላይ ለመነጋገር ለየካቲት 9 ቀን 2012 ዓ.ም አስቸኳይ የስብሰባ ጥሪ ማድረጉን  ቋሚ ሲኖዶስ አስታውቋል።

አስቸኳይ ጉዳይ ካልገጠመው በስተቀር የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዐተ ጉባኤ በዓመት ሁለት ጊዜ (ጥቅምት እና ግንቦት) የሚካሄድ እና በቤተክርስቲያኒቱ መንፈሳዊ እና ማኅበራዊ ጉዳዮች ላይ የመጨረሻ ውሳኔ ሰጪ አካል ነው።

የቅዱስ ሲኖዶስ አስቸኳይ ምልዐተ ጉባኤ ቤተክርስቲያኗንና ምዕመናኑን የሚመለከቱ ጊዜ በማይሰጣቸው አጣዳፊ ጉዳዮች ላይ የእርምጃ ውሳኔዎችን ሊያሳልፍ እንደሚችል አባይ ሚዲያ ያገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡