አባይ ሚዲያ የካቲት 03፤2012

የ19 ዓመቷ ኤደን አለነ በግንቦት ወር ኔዘርላንደ ሮትርዳም ለሚካሄደው አለምአቀፍ የኢሮቪዥን የሙዚቃ ውድድር ላይ እስራኤልን ወክላ የምትወዳደር የመጀሪያዋ ሴት ሆኗለች ኤደን የመጨረሻ ውድድሯን ያደረገችው በቢዮንሴ ሃሎ ዘፈን ሲሆን በህዝብ ምርጫ እና በዳኞች ውሳኔ ለማሸነፍ በቅታለች፡፡

እስራኤልን በመወከል ውድድሩ ላይ ጥሩ ነገር እሰራለሁ ስተል ቃል የገባችው ኤደን ለዚህ ውጤት እንድትበቃ ለመረጧት ምስጋናዋን አቅርባለች፡፡

የእስራኤሉ ጠ/ሚር ቤኒያሚን ናትኒያሁ በትዊተር ገጻቸው የእንኳን ደስ አለሽ መልእክት አስተላለፈው በኢሮቪዥን አሸናፊ እንድትሆን መልካም እድል ተመኝተዋል ኤደን ለሁለት ዓመታት ያህል በእየሩሳሌም የወጣቶች ኳየር ቡድን ውስጥ እንደነበረች መረጃዎች ያሳያሉ፡፡