አባይ ሚዲያ የካቲት 03፤2012

የኢትዮጵያ ሴቶች ህግ ባለሙያ ማህበር ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንዳስታወቀው በሴቶች ላይ የሚፈፀመው ጥቃት መልካቸውን እየቀየሩ እና እየጨመሩ ለመምጣታቸው በደምቢዶሎ የታገቱት ሴት ተማሪዎች አንድ ማሳያ ነው ብሏል በመሆኑም በሴቶቹ ላይ አስካሁን የተፈፀመው ብቻ ሳይሆን ወደ ፊት የሚፈፀመውም ያሳስበናል ብሏል።

የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ጥምረት ድርጅት ዋና ዳይሬክተር አቶ መሱድ ገበየሁ በበኩላቸው በደምቢዶሎ የታገቱት ሴት ተማሪዎች በተመለከተ ሆነ በሌላ ተመሳሳይ ችግር ላይ የብዙሃን ማህበራት ጥቃት በተፈፀመበትና ግጭት በተነሳ ጊዜ መመርመር ፣ መሰነድና ማሳወቅ ካልሆነ በቀር ቀጥታ ሚና የለንም ብለዋል።