አባይ ሚዲያ የካቲት 03፤2012

ሠሞኑን በድንበር አካባቢ የተሰማውና ተግባራዊ እየሆነ ያለው የኤርትራ ስደተኞችን ያለመመዝገብ ሂደት ቢቢሲ ያነጋገራቸው ስደተኞችን አስጨንቋል።

ኤርትራውያን ከሀገራቸው ወጥተው ወደ ኢትዮጵያ ሲገቡ በድንበር አካባቢ ምዝገባ እንደሚደረግ ይታወቃል። ከዚያ በኋላም ወደ ምዕራብ ትግራይ እንዳ’ባጉና ከተማ ይመጡ ነበር።

እዚህ ስፍራም ስለግለሰቦቹ አስፈላጊው መረጃ ከተጠናቀረ በኋላ ወደ ስደተኞች መጠለያ እንዲገቡ የሚደረግበት አካሄድ ነበር።

ዛላንበሳ ድንበር ፋፂ ከተማ እስካሁን ኤርትራውያን ስደተኞችን እየመዘገቡ ሲያስገቡ የነበሩ የፌደራል መንግሥት የስደተኞችና የስደት ተመላሾች ተቋም ሠራተኞች ‘አንመዘግብም’ ማለታቸውን ቢቢሲ ከስደተኞቹ መረዳት ችሏል።