አባይ ሚዲያ የካቲት 03፤2012

የወልቃይት ጠገዴ የአማራ ማንነት እና ወሰን አስመላሽ ኮሚቴ ከምዕራብ አርማጭሆ ህዝብ ጋር በመምከር ሁለት ንዑስ ኮሚቴዎችን ማዋቀሩን አስታወቀ።

የወልቃይት ጠገዴ የአማራ ማንነት እና ወሰን አስመላሽ ኮሚቴ በዛሬው እለት የካቲት 3 ቀን 2012 ዓ.ም በምዕራብ ጎንደር ዞን ከምዕራብ አርማጭሆ ህዝብ ጋር በአብርሀ ጅራ ከተማ ምክክር አድርጓል።

መድረኩን የመሩት የኮሚቴው ምክትል ሊቀመንበር አቶ ጌጤ አዳል፣የህዝብ ግንኙነት ኃላፊው አቶ ክብረአብ ስማቸው እና የኮሚቴው አማካሪ አቶ ገብያው ላቀው ሲሆኑ ከጠለምት የአማራ ማንነትና ወሰን አስመላሽ ኮሚቴም መ/ር ገብረ ኪዳን ተገኝተዋል።