አባይ ሚዲያ የካቲት 04፤2012

በማዕድንና ነዳጅ ሚኒስቴር የሕግ ጉዳዮች ተጠባባቂ ዳይሬክተር አቶ ባምላክ አለማየሁ በሰጡት ማብራሪያ የፌዴሬሽን ምክር ቤት በቅርቡ በወሰነው መሠረት ከሐምሌ 1ቀን 2013 ዓ.ም ጀምሮ ከማዕድንና ነዳጅ ተፈጥሮ ሀብቶች ከሚገኘው ገቢ ውስጥ 50 በመቶው ሀብቱ ለመነጨበት ክልል ልማት ይውላል፡፡

ከ50 በመቶው ውስጥ 10 በመቶው ደግሞ ማዕድኑ ወይም ነዳጁ ለተገኘበት ስፍራ ወይም ኩባንያው ፈቃድ ለወሰደበት ወረዳ ከቀሪው 50 በመቶ ላይ 25 በመቶው ለፌዴራል መንግሥት ገቢ ይደረጋል፡፡ ቀሪው 25 በመቶ ደግሞ የተፈጥሮ ሀብቱ ላልተገግኘባቸው ሌሎች ክልሎች እንዲከፋፈል ምክር ቤቱ ውሳኔ አሳልፏል።