አባይ ሚዲያ የካቲት 04፤2012

የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራዎች ኮርፖሬሽን ሠራተኞች የጥር ወር ደመወዝ ስላልተከፈላቸው በከፍተኛ ችግር ላይ እንደሚገኙ ገለጸዋል፡፡

የኮርፖሬሽኑ ሠራተኞች ለሪፖርተር እንደገለጹት ደመወዝ ሳይከፈላቸው ከአሥር ቀናት በላይ በመቆየታቸው የቤት ኪራይ፣ የልጆች ትምህርት ቤት ክፍያዎችና የቀለብ መሸመቻ ጭምር ችግር ገጥሟቸዋል፡፡

ኮርፖሬሽኑን በተደጋጋሚ ቢጠይቁም ተገቢ ምላሽ የሚሰጣቸው ማጣታቸውን የተናገሩት ሠራተኞች፣ ቀደም ብለው በነበሩ አመራሮች ወቅት የነበረ ውዝፍ የገቢዎች ሚኒስቴር ዕዳ  ስለተከፈለ ገንዘብ አለመኖሩ እንደተነገራቸው አስረድተዋል፡፡

ኮርፖሬሽኑ በበኩሉ የመንገድ ጥገና ዲስትሪክቶችን የመለየት ሥራ ውስጥ መቆየቱን ገልጾ፣ ደመወዛቸው ማክሰኞ የካቲት 3 ቀን 2012 ዓ.ም. ወደ ባንክ መላኩን ገልጿል፡፡