አባይ ሚዲያ የካቲት 04፤2012

ጠቅለይ ሚኒስትሩ በዚሁ ጉዟቸው ከሰባት የመካከለኛው ምስራቅ አገራት ከተውጣጡ ከ15 ሺህ በላይ ኢትዮጵያዊያን እና ትውልደ ኢትዮጵያዊያን ጋር ውይይት እንደሚያደርጉ የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ዛሬ በሰጠው መግለጫ አስታውቋል።

የውይይቱ ዋና አላማም ዜጎች በሚኖሩበት አገር ጥቅማቸው እና ክብራቸው ተጠብቆ እንዲኖሩ ለማድረግና ያሉባቸውን ችግሮች መፍታት በሚቻልበት ጉዳይ ዙሪያ ለመምከር ነው ተብሏል።

በጋራ ከሚኖረው ውይይት በተጨማሪም በተናጠል ከተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ከተወጣጡ ኢትዮጵያዊያን ጋር ውይይት እንደሚደረግ የተገለጸ ሲሆን የዚህ ውይይት አላማም የሚነሱ ጥያቄዎችን ለመመለሥ በሚቻልበትን መንገድ ማመቻቸት መሆኑን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።