አባይ ሚዲያ የካቲት 04፤2012

ኢትዮጵያዊቷ ሎዛ አበራ ትላንት ምሽት ሦስት ግቦችን በማስቆጠር ሀትሪክ ሠርታለች።

በማልታ የሴቶች እግር ኳስ ሊግ ለቢሪኪርካራ እየተጫወተች የምትገኘው ሎዛ አበራ ክለቧ ሞስታን አስተናግዶ 9ለ0 ሲያሸነፍ ሦስት ግቦችን በማስቆጠር ሀትሪክ መሥራት ችላለች።

ተጫዋቿ በተጋጣሚው ሞስታ ክለብ ላይ በአጠቃላይ 26 ግቦች ስታስቆጥር በአጠቃላይ በማልታ ቆይታዋ ደግሞ 30 ግቦችን ከመረብ ላይ ማሳረፍ ችላለች።

ክለቧ ቢሪኪርካራ ዘንድሮ በሊጉ እስካሁን ካደረጋቸው 14 ጨዋታዎች ውስጥ 13ቱን በማሸነፍ እና 40 ነጥብ በመሰብሰብ ሊጉን እየመራ ነው።