አባይ ሚዲያ የካቲት 04፤2012

በሀረሪ ክልል ለግጭት መንስኤ የሚሆኑ እንቅስቃሴዎችን የመግታትና ወንጀልን የመከላከል ተግባራት መከናወናቸውን የክልሉ የፀጥታ ምክር ቤት አስታውቋል።

በተለይም ባለፉት ሁለት ወራት በመሬት ወረራ፣ በጥምቀት በዓል ማክበር ወቅት ከተፈጠረው ችግር ጋር በተያያዘና በሌሎች ወንጀሎች የተጠረጠሩ በርካታ ግለሰቦችን በቁጥጥር ስር ማዋል መቻሉንም ፖሊስ አስረድቷል።

ከጥምቀት በዓል አካባበር ጋር ተያይዞ በተፈጠረው የፀጥታ ችግር ተጠርጥረው ከተያዙ 168 ግለሰቦች መካከል 138ቱ ጉዳያቸው ተጣርቶ መለቀቃቸውንም ተናግረዋል።

በተመሳሳይ በወቅቱ ተሰርቀው ከነበሩ 18 የባለ ሶስት እግር ተሽከርካሪዎች መካከል 17ቱን ማስመለስ መቻሉንም ነው የተናገሩት።