አባይ ሚዲያ የካቲት 04፤2012

የብልጽግና ፓርቲ ከፍተኛ አመራር የሆኑት አቶ ታዬ ደንደአ በቢሸፍቱ ከተማ ውስጥ ከፍተኛ መጠን ያለው ብርና ሌሎች ውድ ንብረቶች ዝርፊያ እንደተፈጸመባቸው ለቢቢሲ ተናገሩ ከብር በተጨማሪም በመኪናቸው ውስጥ ‘ላፕቶፕ’ ኮምፕዩተርና ለስራና ለግል ጉዳይ የሚጠቀሙባቸው ሁለት የማስታወሻ ደብተሮችም መዘረፋቸውን ገልጸዋል።

ዝርፊያው የተፈፀመበት ሁኔታ ሲያስረዱም፤በቢሾፍቱ ከተማ “ቢን ኢንተርናሽናል ሆቴል” መኪናቸውን አቁመው ለምሳ መግባታቸውን የተናገሩ ሃላፊው የመኪናቸው በር በ’ማስተር’ ቁልፍ ተከፍቶ ዝርፍያ መፈጸሙንም አስታውቀዋል።

ይህ ከፍተኛ መጠን ያለውን ገንዘብ በቢሾፍቱ ከተማ ስልጠና እየተሰጠ መኖሩንና ገንዘቡም ለሰልጣኞች አበል የሚሰጥ መኖሩንም አቶ ታየ አስረድተዋል ዝርፍያው ከተፈጸመ በኋላ የአቶ ታየ የማስታወሻ ደብተር በእጄ ገብቷል ብሎ በፌስቡክ ገጹ የጻፈ ሰው እንደነበረና ይህንን ጉዳይ ደግሞ አቶ ታየ ወደ ህግ መውሰዳቸውን ተናግረዋል።

የአቶ ታየ ደንደአ የማስታወሻ ደብተር በእጄ ገብቷል ብሎ ጽፏል የተባለው ግለሰብ በማህበራዊ ሚድያ በፖለቲካዊ ጉዳዮች ላይ አስተያየት በመስጠት የሚታወቅ ደረጀ ቢጌ የተባለ ግለሰብ ነው ተብሏልንበዚህ ዙሪያ ቢቢሲ ለአቶ ደረጀ ያነጋገረው ቢሆንም የማስታወሻ ደብተሩ ይዘት በ’ኢንቦክስ’ ስለተላከልኝ ነበር የማስታወሻ ደብተሩ መዘረፋቸውን የገለጽኩት ብሏል።

“በውስጥ ነው የተላከልኝ ስፖስተውም በውስጥ በኢንቦክስ እንደተላከልኝ ገልጫለሁ” ሲል አቶ ታየ ስለመሰረቃቸውን ግን የማውቀው ነገር የለም በማለት አቶ ደረጀ አስተባብሏል የቢሾፍቱ ከተማ ፖሊስ ስለጉዳዩ ተጠይቆ ምርመራ እየተካሄደ ስለሆነ ተጣርቶ ሲያልቅ ይፋ እንደሚደረግ የከተማው ፖሊስ አዛዥ ኮማንደር ደረጀ ሙለታ ገልጸዋል።

አቶ ታዩ ደንደአ የብልጽግና ፓርቲ ከፍተኛ አመራር ሲሆኑ በመገናኛ ብዙሃንና በማህበራዊ ሚዲያዎች በተለያዩ ርእሰ~ጉዳዮች ላይ የፓርቲያቸውንና የራሳቸውን አቋም በመግለጽ የሚታወቁ ናቸው።