አባይ ሚዲያ የካቲት 04፤2012

ለሁለት ሳምንታት ሲካሄድ የቆየውን የብልጽግና ፓርቲ አመራሮች ሥልጠና የመዝጊያ መርሀ ግብር ላይ መልዕክት ያስተላለፉት የብልጽግና ፓርቲ ሊቀመንበር ዶክተር አብይ አህመድ፤ ‹‹የተሰጣችሁ ቦታ ሁልጊዜ ከእናንተ ጋር የሚቆይ ስላልሆነ ባላችሁ የሀላፊነት ጊዜ ህዝባችሁን አገልግላችሁ እለፉ›› ብለዋል፡፡

አመራሩ የብልፅግና ፓርቲ መመሪያዎችንና ፖሊሲዎችን አውቆ ሁልጊዜም ዝግጁ እየሆነ ሊሄድ እንደሚገባም አሳስበዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ እንዳሉት፤ የስልጠናው ዋና ዓላማ የብልጽግና ፓርቲ አመራሮች እንዲተዋወቁ፣ እንዲተማመኑና አንዱ ሌላውን የሌላውን ብቃት መገንዘብ እንዲችል ፎረም መፍጠር ሲሆን፤ ትውውቁ ሙሉ በሙሉ በሚፈለገው ደረጃ ተከናውኗል ባይባልም የዓላማውን ግንዛቤን መፍጠር ችሏል፡፡