አባይ ሚዲያ የካቲት 04፤2012

በሊቢያ የሚገኘው አለማቀፉ የስደተኞች ድርጅት ከሊቢያ ምዕራባዊ የውሃ ክፍል በኩል ወደ አውሮፓ በመጓዝ ላይ የነበሩ 81 ስደተኞቸ በሊቢያ የባህር ድንብር ጠባቂዎች አማካይት መትረፋቸውን አስታውቋል፡፡

ከ81 ስደተኞች መካካል 18ቱ ሴቶች ሲሆኑ አራቱ ደግሞ ህፃናት ናቸው ተብሏል፡፡

ስደተኞቹ የጤና ምርመራ እና አስቸኳይ እርዳታ ተደርጎላቸው ወደ ትሪፖሊ መመለሳቸውም ተነግሯል፡፡

እንደ አለማቀፉ የስደት ድርጅት (አይ ኦ ኤም) መረጃ በሊቢያ ከ600ሺህ በላይ ስደተኞች ይገኛሉ፡፡ አብዛኞቹ ስደተኞችም የሰብዓዊ እርዳታ ያስፍልጋቸዋል፡፡

ምንም እንኳን ድርጅቱ ሊቢያ ለስደተኞች ምቹ አለመሆናን በተደጋጋሚ ጊዜ ቢገልፅም ከጎርጎሮሳውያኑ 2011 ወዲህ ጠንካራ ማዕከላዊ መንግስት መመስረት የተሳናት ሊቢያ አሁንም ለህገ ወጥ ስደተኞች ተመራጭ እንደሆነች ቀጥላለች፡፡