አባይ ሚዲያ የካቲት 05፤2012

ኢትዮጵያዊው አትሌት ሳሙኤል ተፈራ በተያዘው የፈረንጆቹ ዓመት በአንድ ማይል ርቀር ሩጫ ሁለተኛውን የዓለም ፈጣን ሰዓት አስመዝግቧል።

ትላንት በአየርላንድ አትሎን የአንድ ማይል የቤት ውስጥ ውድድር ሲካሄድ አትሌት ሳሙኤል ተፈራ ርቀቱን በ3 ደቂቃ ከ55 ሰከንድ ከ86 ማይክሮ ሰከንድ በሆነ ጊዜ በማጠናቀቅ ውድድሩን አሸንፏል።

በዚህም በፈረንጆቹ 2020 በአንድ ማይል የቤት ውስጥ ውድድር ሁለተኛውን ፈጣን ሰዓት ማስመዝገብ ችሏል።

ስኮትላንዳዊው ስኮት ኦሃር ርቀቱን በ3 ደቂቃ 55 ሰከንድ ከ61 ማይክሮ ሰከንድ በመጨረስ የወቅቱ ፈጣን ሰዓት ባለቤት ነው።