አባይ ሚዲያ የካቲት 05፤2012

ከተማ አስተዳደሩ ከመኖሪያ ቤት፣ ከኢንቨስትመንት እና መሠረተ ልማትን ከማስፋፋት ጋር በተያያዘ በተደጋጋሚ ጥያቄዎች ይነሱበታል፡፡

ይሁን እንጂ ከካሳ ክፍያ ጋር በተያያዘ ለሚነሱ ጥያቄዎች ምላሽ መስጠት አልቻለም፡፡

የደብረ ብርሃን ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ደጀኔ ተሾመ እንደተናገሩት ደግሞ ከተማ አስተዳደሩ መሬትን ከሦስተኛ ወገን ነጻ ለማድረግ ገንዘብ አዘጋጅቶ እየጠበቀ ቢሆንም አዋጁ መመሪያና ደንብ ስላልተዘጋጀለት ተግባራዊ ማድረግ አልተቻለም፡፡

በመኖሪያ ቤት ከተደራጁ 1ሺህ 90 የተለያዩ የኅብረት ሥራ ማኅበራት መካከል 633 የሚሆኑት መስፈርቱን አሟልተው ቦታ በመጠባበቅ ላይ ይገኛሉ፡፡