አባይ ሚዲያ የካቲት 07፤2012

ለጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐብይ አህመድ የናይጄሪያው አቡጃ ዩኒቨርሲቲ አስተዳደር የክብር ዶክትሬት ሊሰጥ መሆኑን አስታወቀ፡፡

የዩኒቨርሲው ምክትል ሊቀመንበር ፕሮፌሰር አብዱል ራሺድ ናላህ እንደገለፁት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ለሽልማቱ የታጩት በአገራቸው እና በኤርትራ ለተፈጠረው ሰላም ያበረከቱትን አስተዋፅኦ ከግምት ውስጥ በማስገባት ነው፡፡

የናይጄሪያ ኒውስ ዘገባ እንዳመለከተው ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ በተጨማሪ ጡረተኛው የቀድሞ የጦር ሚኒስትር ጀኔራል አልዋሊ ካዚር እና ድምፃዊው ኢብራሂም ናራምባዳ በየዘርፋቸው ላበረከቱት አስተፅኦ ለሽልማት መታጨታቸው ታውቋል ዊው ኢብራሂም ናራምባዳ በየዘርፋቸው ላበረከቱት አስተፅኦ ለሽልማት መታጨታቸው ታውቋል፡፡