አባይ ሚዲያ የካቲት 07፤2012

በአፍሪካ ውስጥ የመጀመሪያው በኮሮና ቫይረስ መያዙ የተረጋገጠ ህመምተኛ ግብጽ ውስጥ መገኘቱ ተነገረ የግብጽ የጤና ሚኒስቴር እንዳስታወቀው በሽታው የተገኘበት ግለሰብ የውጪ አገር ዜግነት ያለው መሆኑን ቢገልጽም ከየት አገር እንደመጣ ግን አላመለከተም።

የአፍሪካ አገራት ከቻይና ጋር ባላቸው የጠበቀ ግንኙነት ምክንያት በሽታው በአጭር ጊዜ አፍሪካ ውስጥ ሊታይ እንደሚችል የጤና ባለሙያዎች ቀደም ሲል ሲያስጠነቅቁ ነበር።

ከቻይናዋ የዉሃን ከተማ ተነስቶ ወደ ተለያዩ አገራት የተዛመተው ይህ በሽታ እስካሁን ድረስ ከ1ሺህ 500 በላይ ሰዎችን ህይወት ቀጥፏል።