አባይ ሚዲያ የካቲት 08፤2012

በተባበሩት አረብ ኤምሬቶች በህገ ወጥ መንገድ የሚኖሩ 10 ሺ ኢትዮጵያውንን ህጋዊ ለማድረግ ከስምምነት ተደረሰ፡፡

በስምምነቱ መሠረትም የጉዞ ሰነድ በማጣት እና በከፋ ችግር ውስጥ ሆነው ከሀገር እንዳይወጡ ለዓመታት ተከልክለው የቆዩ 135 ኢትዮጵያንን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ይዘው ይመለሳሉ።

ከአርብ ጀምሮ በሀገሪቱ የስራ ጉብኝት በማድረግ ላይ የነበሩት ጠቅላይ ሚኒስትሩ የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች ጉብኝታቸውን ዛሬ አጠናቀዋል።

በጉዞው በተደረገ የዲፕሎማሲ ስራ በአቡዳቢ ለኢትጵዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ህንጻ ማሰሪያ ቦታም ከመፈቀዱም ባለፈ ለኢትዮጰያውያን ትምህርት ቤት ለመክፈት ከስምምነት ተደርሷል።