አባይ ሚዲያ የካቲት 08፤2012

የድምጻዊ ቴዎድሮስ ካሳሁን(ቴዲ አፍሮ) ኢትዮጵያ ወደ ፍቅር የተሰኘው የሙዚቃ ድግስ ቅዳሜ የካቲት 14 በመስቀል አደባባይ እንደሚካሄድ የሚታወቅ ሲሆን የአቡጊዳ ባንድ አባላት እና የሳውንድ ኢንጂነሩ ከውጪ ሃገር ወደ ሃገር ውስጥ መግባታቸውን እና ልምምድ መጀመራቸውን  ማናጀሩ አቶ ጌታቸው ማንጉዳይ ለታዲያስ አዲስ ተናግሯል፡፡

ድምጻዊው በመድረክ ላይ ለ3 ሰአታት ቆይታ እንደሚያደርግ ሲሆን የመግቢያ ዋጋውም ቪ.አይ.ፒ 500 ብር መደበኛ ደግሞ 200 ብር መሆኑንም ገልጧል፡፡

ከፋሲካ በኋላም በጎንደር እና አርባ ምንጭ ከተሞች ተመሳሳይ የሙዚቃ ዝግጅቶችን ለማቅረብ ዝግጅቶች እየተከናወኑ መሆኑን የድምጻዊው ማናጀር አስታውቋል፡፡