አባይ ሚዲያ የካቲት 08፤2012

የኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ቡድን የመጀመሪያው ችቦ በአዲስ አበባ በይፋ ተለኮሰ።

የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴም የኦሎምፒክ ቡድኑን የቶክዮ 2020 የመጀመሪያውን ችቦ በይፋ ለኩሰዋል።

በዚህም ወቅት ባስተላለፉት መልዕክት “እኛ ኢትዮጵያውያን በተባባረ አንድነትና ህብረት ወደ ላቀ ብልፅግና እንደርሳለን፤ ኢትዮጵያ ብዙ ጀግኖች ታፈራለች” ብለዋል።

የኢትዮጵያ መንግስት ለኦሎምፒክ ቡድኑ ድጋፉን በኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ አሳይቷል ያሉት ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ፥ “እኔም ባለኝ አቅም ሁሉ እደግፋለሁ” ነው ያሉት።

በተመሳሳይ ሰባተኛው ከተማ አቀፍ የብዙሃን ስፖርት በዛሬው ዕለት በመስቀል አደባባይ ተካሂዷል፡፡