አባይ ሚዲያ የካቲት 08፤2012

በኮሮና ቫይረስ የሚያዙ አዳዲስ ሰዎች ቁጥር እየቀነሰ መሆኑን ቻይና ያስታወቀች ሲሆን ይህም ሁኔታ የታየው በባለፉት ሶስት ቀናት መሆኑ ተዘግቧል ባለፈው ሳምንት እሁድ ባለስልጣናቱ 2ሺ 9 አዳዲስ ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸውን እንዲሁም በመላው ሃገሪቱ 142 ሰዎች መሞታቸውን ተናግረው ነበር።

በሳምንቱም መጀመሪያ በቫይረሱ የሚያዙ ሰዎች ቁጥር ማሻቀብ አሳይቶ የነበረ ቢሆንም ከቀናት በኋላ መረጋጋት እንዲሁም ማሽቆልቆል አሳይቷል ብለዋል እስካሁን ባለው መረጃ 68 ሺ ሰዎች በቫይረሱ የተያዙ ሲሆን የሟቾች ቁጥር ደግሞ 1665 ደርሷል።

እስካሁን ባለው መረጃ በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎችን አሳፍራለች ተብላ እንዳትንቀሳቀስ እንዲሁም በለይቶ ማቆያ ያለችው መርከብ በጃፖን ወደብ የምትገኝ ሲሆን፤ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር በከፍተኛ ሁኔታ እያሻቀበ ነው ተብሏል።

የቻይና ማዕከላዊ ባንክ የመገበያያ ገንዘቦችን በኬሚካል የመርጨት እቅድ እንዳለው አስታውቋል። ይህም ቫይረሱ እንዳይዘመት ይረዳዋልም ተብሏል የፈረንሳይ ባለስልጣናት ቅዳሜ እለት አንድ የቻይና ቱሪስት በኮሮና ቫይረስ መሞቱን አሳውቀዋል። ይህንንም ለመጀመሪያ ጊዜ ከእስያ ውጭ የተመዘገበ ሞት ያደርገዋል።

በተለያዩ ሃገራት ማረፍ ተከልክላ የነበረች አንዲት መርከብ በካምቦዲያ ማረፏን ተከትሎ አንዲት አሜሪካዊት በቫይረሱ መያዟ ታውቋል። ግለሰቧ ወደ ማሌዥያ በአውሮፕላን በረራ ባደረገችበት ወቅት ነው ሁኔታው የታወቀው።

ቅዳሜ እለት የአለም አቀፉ የጤና ድርጅት ኃላፊ ዶር ቴድሮስ አድሃኖም ቻይና ለወረርሽኙ የሰጠችውን ትኩረት አድንቀዋል “ቻይና የቫይረሱን መዛመት በመቆጣጠር ሌላው ዓለም እንዲዘጋጅ ጊዜን መለገስ ችላለች፤ ምን ያህል ጊዜ እንዳለን ባናውቅም። ከቻይና ውጭ ባሉ ሃገራት ያለው የመዛመት ሁኔታ ዝቅተኛ መሆኑንም ማየት ተስፋ የሚሰጥ ነገር ነው” ብለዋል።

ከአስር ሚሊዮን በላይ የሚሆኑ ቻይናውያን የቫይረሱን መዛመት ለመቆጣጠር በሚል ከእለት እለት እንቅስቃሴያቸው ተገድበዋል ከፍተኛ ትኩረት የተሰጣት የቫይረሱ መነሻ የሆነቸው የሁቤ ግዛት ውሃን ከተማ ስትሆን፤ በውሃን እንቅስቃሴ ከተገደበ ሳምንታት ተቆጥረዋል፤ ከተማዋም ከሌሎች የሃገሪቱ ክፍሎች ተቆራርጣለች።