አባይ ሚዲያ የካቲት 08፤2012

የጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐብይ አህመድ የተባበሩት አረብ ኢምሬቶች ጉብኝት ኢትዮጵያንና ኢትዮጵያዊያንን ያስከበሩ ተግባራት የተከናወኑበት መሆኑን የፕሬስ ሴክሬተሪያት ኃላፊ አቶ ንጉሱ ጥላሁን ተናገሩ።

የጠቅላይ ሚኒስትሩ ጉብኝት የዜጎች አጠቃላይ ሁኔታን ተረድቶ መብቶቻቸውና ጥቅሞቻቸው እንዲከበርና በዘላቂነት በዜግነታቸው ክብራቸው ተረጋግጦ እንዲኖሩ ለማድረግ ነው ሲሉም አክለዋል።

በተባበሩት አረብ ኤምሬቶች የኢትዮጵያ አምባሳደር ሱለይማን ደደፎ በበኩላቸው ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከአገሪቱ  የመንግስት ኃላፊዎች ጋር ያደረጉት ውይይት ውጤታማ እንደነበር ገልጸዋል።

አስቀድሞ 300 ከሚሆኑ የኮሚኒቲ አመራሮች፣ ከአምባሳደሮች፣ ከቆንስላ ጽህፈት ቤቶችና ሌሎችም ጋር በችግሮቹ ላይ አስቀድመው መወያየታቸውን አቶ ንጉሱ ገልጸዋል።