አባይ ሚዲያ የካቲት 17፤2012

ባለፉት ስድስት ወራት ብቻ ከ1ነጥብ 6 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት የኬብል ስርቆት መፈፀሙን የጥገና ማዕከል ዋና ዳይሬክተር አቶ ታመነ ሽመልስ ተናግረዋል ባለፉት አራት ቀናት ከልደታ እስከ ስታዲየም ባለው የባቡር መስመር የሲግናል ኮሙኒኬሽን ኬብል ተቆራርጦ መገኘቱም ገልጸዋል።

ከዚህ ቀደም የመብረቅ መከላከያ፣ ለኮሙኒኬሽንና ለሌሎች ተግባራት የሚውሉ ገመዶች ስርቆት በተደጋጋሚ ተፈጽሟል”በዚህም ሳቢያ አገልግሎት ለመስጠት ዝግጁ በሆኑ ባቡሮች ሙሉ በሙሉ አገልግሎት መስጠት አልተቻለም” ብለዋል ዋና ዳይሬክተሩ።