አባይ ሚዲያ የካቲት 22፤2012

ቀነኒሳ የሞ ፋራህን የግማሽ ማራቶን ክብረ-ወሰን ሰበረ::

በለንደን ከተማ በተካሄደው የቫይታሊቲ ቢግ ግማሽ ማራቶን፤ ቀነኒሳ በቀለ ክብረ-ወሰን በመስበር አሸንፏል።

ለመጀመሪያ ጊዜ በውድድሩ የተሳተፈው የ5 ሺህ እና 10 ሺህ ሜትር ውድድሮች የዓለም ክብረ ወሰን ባለቤቱ ቀነኒሳ ውድድሩን 1ሰአት ከ22ሰከንድ በሆነ ጊዜ በመግባት በእንግሊዛዊው ሯጭ ሞ ፋራህ የተያዘውን የቫይታሊቲ ቢግ ግማሽ ማራቶን ክብረ-ወሰን ሰብሯል።

ከቀነኒሳ ጋር ይፋጠጣል ተብሎ የተጠበቀው ሞ ፋራህ ከጥቂት ቀናት በፊት በህመም ምክንያት እንደማይሳተፍ አሳውቆ ነበር።