አባይ ሚዲያ የካቲት 24፤2012

የሶማሌው ፕሬዚዳንት ሙስጠፌ ዑመር ወንድም ጥቃት ደረሰባቸው፡፡

የሶማሌ ክልል ፕሬዚዳንት ሙስጠፌ ዑመር ወንድም የሆኑት ዶ/ር አብዱራህማን ዑመር ትላንት ማምሻውን በደገህቡር ከተማ በጩቤ ተወግተው ለህክምና ሆስፒታል ገብተዋል።

ዶ/ር አብዲራህማን የደጋህቡር ሆስፒታል ሜዲካል ዳይሬክተር ሲሆኑ ከመኪና ወርደው ፀጉር ቤት ለመግባት የመኪናውን በር እንደዘጉ በደፈጣ ሲጠብቃቸው የነበረው ግለሰብ ዘሎ ጥቃት ማድረሱን የአይን እማኞች ገልፀዋል።

ድርጊቱን የፈፀመው ግለሰብ በፖሊስ ቁጥጥር ስር ውሎ ጉዳዩ በምርመራ ላይ እንደሚገኝ የደረሰን መረጃ ያመለክታል።

ፕሬዚዳንት ሙስጠፌ ዑመር በቀድሞ ስርዓት ወንድማቸው ፋይሰልን ዑመርን ማጣታቸውና ማንም ላይ በቀል አልፈልግም በእኔ ላይ የደረሰው በሁሉም ላይ ደርሷል ስለዚህ ይቅር መባባል አለብን ማለታቸው ይታወሳል።