አባይ ሚዲያ የካቲት 24፤2012

በባየርሙኒክ የታዳጊዎች ውድድር ኢትዮጵያን ወክለው የሚሳተፉ ተጫዋቾች ተመረጡ፡፡

ዘጠነኛው የባየርሙኒክ የታዳጊዎች ውድድር ከሚያዚያ 29 እስከ ግንቦት 2 ቀን 2012 ዓ.ም የሚካሄድ ይካሄዳል፡፡

በውድድሩ ላይ ኢትዮጵያን ወክሎ የሚሳተፈውን ቡድን ለመምረጥ የካቲት 19 እና 20 ቀን 2012 ዓ.ም በአዲስ አበባ ስታዲየም ከ16 ዓመት በታች የታዳጊዎች ውድድር መካሄዱ የሚታወስ ነው።

በመምረጫ ውድድሩ ላይ ከኢትዮጵያ የተለያዩ ክፍሎች የተወጣጡ 16 ቡድኖች ተሳትፈዋል።

ከ16 ቡድኖች ውስጥ የተሻለ ብቃት ያላቸው10 ተጫዋቾች መመረጣቸውን የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የወጣት ክፍል ባለሙያ አቶ ያሬድ አለማየሁ ገልጸዋል።

ቢንያም ንጉሴ፣ፉአድ አብዱራህማን፣አሸናፊ አስፋው፣ጀማል መሐመድ፣አቡበከር አክሊሉ፣ያሬድ አበራ፣ትንሳኤ ሽፈራው፣ሄኖክ ካሳ፣ናታን ንጉሴ እና አስጨናቂ ገበያው በውድድሩ ላይ ኢትዮጵያን ወክለው የሚሳተፉ ተጫዋቾች ናቸው።