አባይ ሚዲያ የካቲት 25፤2012

በአዲሱ የምርጫ እና የፖለቲካ ፓርቲዎች አዋጅ መሰረት የተመዘገቡ ፓርቲዎች ሶስት ብቻ መሆናቸውን ምርጫ ቦርድ አስታወቀ።

ቦርዱ እንዳስታወቀው በአዲሱ የምርጫ እና የፖለቲካ ፓርቲዎች አዋጅ መሰረት ሁሉም አገር አቀፍ እና ክልላዊ ፓርቲዎች በቀጣዩ ምርጫ ለመሳተፍ የግድ ዳግም ምዝገባ ማድረግ አለባቸው።

በዚህ አዋጅ መሰረት ፓርቲዎች በአገር አቀፍ ደረጃ ለመመዝገብ 10 ሺህ አባላት ማስፈረም አንዲሁም በክልል ደረጃ ለመመዝገብ ደግሞ 4 ሺህ እና ከዚያ በላይ ፊርማ ማሰባሰብ አለባቸው።

ዳግም ምዘገባው ደግሞ እስከ መጋቢት 3 ቀን 2012 ዓ.ም ድረስ ብቻ ቢሆንም አስካሁን በአዲሱ አዋጅ መሰረት የተመዘገቡት አረና፣ህወሃት እና ትዴት ብቻ ሲሆኑ ሶስቱም ክልላዊ ፓርቲዎች ናቸው።

በዚህ አዋጅ መሰረት ለመመዝገብ በሂደት ላይ ካሉ ፓርቲዎች ደግሞ በድምሩ ሰባት ፓርቲዎች ብቻ መሆናቸውንም ቦርዱ አስታውቋል።