አባይ ሚዲያ የካቲት 26፤2012

በምስራቅ ወለጋ ዞን በእሳት አደጋ በሰውና ንብረት ላይ ጉዳት ደረሰ በኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ወለጋ ዞን ሲቡ ስሬ ወረዳ ስሬ ከተማ በደረሰ የእሳት አደጋ በሰው እና በንብረት ላይ ጉዳት መድረሱ ተሰምቷል በእሳት አደጋው በ15 ሰዎች ላይ ከባድ የአካል ጉዳት መድረሱን የሲቡ ስሬ ወረዳ የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ፅህፈት ቤት አስታውቋል።

በአደጋው ጉዳት ከደረሰባቸው ሰዎች ውስጥ 3 ሰዎች ለህክምና ወደ አዲስ አበባ ሪፈር የተደረጉ ሲሆን፥ 2 ሰዎች ደግሞ ወደ ነቀምቴ ሆስፒታል እንዲሁም ቀሪዎቹ 10 ሰዎች ደግሞ በስሬ ሆስፒታል ህክምና እየተከታተሉ ይገኛሉ ተብሏል።

በተጨማሪም በእሳት አደጋው 15 የሚሆኑ የአልባሳት፣ የጫማ፣ የሞባይል ስልክ ቤቶች እንዲሁም የሸቀጣ ሸቀጥ መደብሮችን ጨምሮ መኖሪያ ቤቶች ተቃጥለዋል ቃጠሎ በደረሰባቸው በንግድ እና የመኖሪያ ቤቶች ውስጥ የነበሩ ንብረቶችም ሙሉ በሙሉ መውደማቸው ተነግሯል የእሳት አደጋው መንስኤ እስካሁን እየተጣራ መሆኑን ከወረዳው የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ፅህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።